ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ።
ዘኍል 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ የምመርጠው ሰው በትርም ታቈጠቍጣለች፤ እስራኤላውያን በእናንተ ላይ ነጋ ጠባ የሚያደርጉትንም ማጕረምረም በዚህ እገታለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቁጣለች፥ በእናንተም ላይ ያጉረመረሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ እኔ ለክህነት የምመርጠው ሰው በትሩ በማቈጥቈጥ ትለመልማለች፤ በዚህም ዐይነት እነዚህ እስራኤላውያን በየጊዜው በአንተ ላይ ማጒረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቍጣለች፥ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ። |
ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ።
የእግዚአብሔርንም ክብር ጥዋት ታያላችሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ያንጐራጐራችሁትን ሰምቶአልና፤ በእኛም ላይ የምታንጐራጕሩ እኛ ምንድን ነን?” አሉ።
በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ።
ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
ቤቶችሽንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙም ሴቶች ፊት ይበቀሉሻል፤ ግልሙትናሽንም አስተውሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ዋጋ አትሰጪም።
ሴሰኝነትሽንም፥ ከግብፅ ምድር ያወጣሽውን ዝሙትሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፤ ዐይንሽንም ከእንግዲህ ወዲህ ወደ እነርሱ አታነሺም፤ ግብፅንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።
ድንኳንዋም ስትነሣ ሌዋውያን ይንቀሉአት፤ ድንኳንዋም ስታርፍ ሌዋውያን ይትከሉአት፤ ሌላ ሰው ግን ለመንካት ቢቀርብ ይገደል።
ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች።
ስለዚህም አንተና ማኅበርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ ታጕረመርሙ ዘንድ አሮን ማንነው?”
ለቆሬም ለማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አላቸው፥ “ነገ እግዚአብሔር የእርሱ የሚሆኑትን፥ ቅዱሳንም የሆኑትን ያያል፥ ያውቃልም፤ የመረጣቸውንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀርባቸዋል።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ ለማይሰሙ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።”
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤ አለቆቻቸውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፤ የበሰለ ለውዝም አፈራች።
አንተ በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስንሻገር የዮርዳኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነዚህ ድንጋዮችም ለእስራኤል ልጆች ለዘለዓለም መታሰቢያ ይሆናሉ።”