Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ቍጣዬ ከእ​ርሱ ዘንድ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ሀገ​ራ​ቸ​ውን አድ​ና​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም እወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ ውብ አበባ ያብባል፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣ ሥር ይሰድዳል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ቁጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ከዳተኝነታቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለእስራኤል ሕዝብ እንደሚወርድ ጠል እሆናለሁ። እነርሱ እንደ አበባ ይፈካሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥር ይሰዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ፥ እንደ አበባም ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ሥሩን ይሰድዳል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 14:5
32 Referencias Cruzadas  

የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ምድረ በዳ ያብ​ባል፤ ሐሤ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ የሊ​ባ​ኖስ ክብ​ርና የቀ​ር​ሜ​ሎስ ክብር ይሰ​ጠ​ዋል፤ ሕዝ​ቤም የጌ​ታን ክብር፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ግርማ ያያሉ።


በሚ​መ​ጣው ዘመን የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሥር ይሰ​ድ​ዳሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ያብ​ባል፤ በፍ​ሬ​ያ​ቸ​ውም የዓ​ለ​ሙን ፊት ይሞ​ላሉ።


በል​ባ​ችሁ ውስጥ በፍ​ቅር ሥር መሠ​ረ​ታ​ችሁ የጸና ሲሆን ክር​ስ​ቶስ በሃ​ይ​ማ​ኖት በሰው ውስጥ ያድ​ራ​ልና።


ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤


አው​ቅም ዘንድ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።


ውኃ በሥሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፥ ጠልም በአ​ዝ​መ​ራዬ ላይ ይወ​ር​ዳል፤


ትም​ህ​ር​ቴ​ንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድ​ር​ገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይው​ረድ፤ በእ​ር​ሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣ​ርም ላይ እንደ ጤዛ።


የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።


በደ​ረቅ መሬት ላይ ለሚ​ሄ​ድና ለተ​ጠማ ውኃን እሰ​ጣ​ለሁ፤ መን​ፈ​ሴን በዘ​ርህ ላይ፥ በረ​ከ​ቴ​ንም በል​ጆ​ችህ ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤


ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እንደ ቀትር ብር​ሃን፥ በአ​ጨ​ዳም ወራት እንደ ጠል ደመና በማ​ደ​ሪ​ያዬ ጸጥታ ይሆ​ናል” ብሎ​ኛ​ልና።


ስለ​ዚ​ህም ትዕ​ቢት ያዛ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ተጐ​ና​ጸ​ፉ​አት።


የዳ​ነው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በጥ​ዋት፥ በማ​ለ​ዳም ፀሐይ ይወ​ጣል፤ ብር​ሃ​ኑም በነ​ግህ ይመ​ጣል፤ ከዝ​ና​ምም የተ​ነሣ በም​ድር ሐመ​ል​ማል ይለ​መ​ል​ማል።


እነሆ፥ አበ​ባ​ዎ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ድጉ ተመ​ል​ከቱ፤ አይ​ፈ​ት​ሉም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሰሎ​ሞን እንኳ በክ​ብሩ ዘመን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ አል​ለ​በ​ሰም።


ሁለቱ ጡቶ​ችሽ መንታ እንደ ተወ​ለዱ፥ በሱፍ አበባ መካ​ከል እን​ደ​ሚ​ሰ​ማሩ እንደ ሚዳቋ ግል​ገ​ሎች ናቸው።


ልጅ ወን​ድሜ የእኔ ነው፥ እኔም የእ​ርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበ​ባ​ዎች መካ​ከ​ልም መን​ጋ​ውን ያሰ​ማ​ራል።


የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው።


አን​ተስ ብት​ሰ​ማኝ የድ​ን​ገት አም​ላክ አል​ሆ​ን​ህም፥ ለሌላ አም​ላ​ክም አት​ስ​ገድ።


ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የሠራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ።


“ሰማይ በላይ ደስ ይበ​ለው፤ ደመ​ና​ትም ጽድ​ቅን ያዝ​ንቡ፤ ምድ​ርም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታብ​ቅል፤ ጽድ​ቅም በአ​ን​ድ​ነት ይብ​ቀል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ከዚ​ህም በኋላ መን​ገ​ዱን አይ​ቻ​ለሁ፤ ፈወ​ስ​ሁ​ትም፤ አጽ​ና​ና​ሁት፤ እው​ነ​ተኛ ደስ​ታ​ንም ሰጠ​ሁት።


በሩ​ቅም በቅ​ር​ብም ላሉ በሰ​ላም ላይ ሰላም ይሁን፤ እፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ከዳ​ተ​ኞች ልጆች ሆይ! ተመ​ለሱ፤ ቍስ​ላ​ች​ሁ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ። እነሆ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ሆ​ና​ለን፤ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህና።


ለእ​ነ​ር​ሱም መል​ካ​ምን በማ​ድ​ረግ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም በፍ​ጹም ልቤና በፍ​ጹም ነፍሴ በዚ​ህች ምድር እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios