ንጉሡም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጣ፤ ከእርሱም ጋር የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ፥ ካህናቱና ነቢያቱም፥ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሾቹ ጀምሮ እስከ ታላቆቹ ድረስ ወጡ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ በጆሮአቸው አነበበ።
ነህምያ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓፊውን ዕዝራን ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ሁሉ ከውሃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ እንደ አንድ ሰው ተሰበሰቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሓፊው ለዕዝራ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ ጌታ ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሐፊው ለዕዝራ ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ በሰባተኛው ወር በየከተሞቻቸው መስፈራቸውን አበቁ፤ በዚያም ወር በመጀመሪያው ቀን በኢየሩሳሌም የውሃ በር ተብሎ በሚጠራው አደባባይ በውስጥ በኩል ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም የሕግ ምሁሩን ዕዝራን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን የኦሪትን ሕግ መጽሐፍ ያመጣላቸው ዘንድ ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፥ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሐፊውን ዕዝራን ተናገሩት። |
ንጉሡም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጣ፤ ከእርሱም ጋር የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ፥ ካህናቱና ነቢያቱም፥ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሾቹ ጀምሮ እስከ ታላቆቹ ድረስ ወጡ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ በጆሮአቸው አነበበ።
ኬልቅያስም ጸሓፊውን ሳፋንን፥ “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤት አግኝቼአለሁ” ብሎ ነገረው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው።
ንጉሡም፥ የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ በጆሮአቸው አነበበ።
ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዐትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።
ንጉሡም አርተሰስታ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቃልና ለእስራኤል የሆነውን ሥርዐት ይጽፍ ለነበረው ለጸሓፊው ለካህኑ ለዕዝራ የሰጠው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው፦
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ፥ በጸሓፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ።
በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።
ሕዝቡም ወጥተው አመጡ፤ እያንዳንዱም በቤቱ ሰገነት ላይ፥ በአደባባዩም ላይ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ላይ፥ በውኃውም በር አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳስ ሠሩ።
በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ በወንዶችና በሴቶች በሚያስተውሉትም ፊት፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
እስራኤል ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ ዘንድ እርሱ በመረጠው ቦታ በአንድነት በሚሄድበት ጊዜ፥ ይህን ሕግ በእስራኤል ሁሉ ፊት በጆሮው አንብበው።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።