ነህምያ 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሜን ሐናኒንና የምሽጉ አዛዥ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ኀላፊነት ሰጠኋቸው፤ እርሱም እውነተኛና ከሌሎች ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም የኢየሩሳሌምን ከተማ ያስተዳድሩ ዘንድ ሁለት ሰዎችን ሾምኩ፤ እነርሱም የእኔ ወንድም የሆነው ሐናኒና የምሽግ ኀላፊ የነበረው ሐናንያ ናቸው፤ ሐናንያ እውነተኛና እግዚአብሔርን በመፍራት ረገድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፥ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። |
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር፥ ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር።
ከወንድሞች አንዱ ሐናኒ፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይሁዳ መጡ፤ እኔም የዳኑትን፥ ከምርኮም የተረፉትን የአይሁድን ነገር፥ የኢየሩሳሌምንም ነገር ጠየቅኋቸው።
በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሓፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም ፈዳያን ሾምሁ፤ ከእነርሱም ጋር የመታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነርሱም የታመኑ ሆነው ተገኙ፤ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።
በቤቱም አጠገብ ላለው ለግንብ በሮች፥ ለከተማውም ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ለንጉሡ ዱር ጠባቂ ለአሳፍ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልሁት። ንጉሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከበረች የአምላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበረችና።
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
እኔም፥ “ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፤ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው፥ አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቂዎችን አስቀምጡ” አልኋቸው።
አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው።