Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እን​ግ​ዲህ በዚህ ከመ​ጋ​ቢ​ዎች እያ​ን​ዳ​ንዱ ቸርና ታማኝ ሆኖ እን​ዲ​ገኝ ይፈ​ለ​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ባለዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከዚህም በላይ፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ያሻል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እንደዚህም ሲሆን፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 4:2
17 Referencias Cruzadas  

ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


ሰነፍ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፤ ብልህ መልእክተኛ ግን ራሱን ያድናል።


አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታ​መነ ነው።


አክ​ር​ጳ​ንም “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾ​ም​ህ​ባ​ትን መል​እ​ክ​ት​ህን እን​ድ​ት​ፈ​ጽ​ማት ተጠ​ን​ቀቅ” በሉት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ስለ እና​ንተ የሚ​ላክ በክ​ር​ስ​ቶስ የታ​መነ፥ የእ​ኛም ወን​ድ​ማ​ች​ንና አገ​ል​ጋ​ያ​ችን ከሚ​ሆን ከኤ​ጳ​ፍ​ራስ ተም​ራ​ች​ኋል።


ስለ ደና​ግ​ልም የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አይ​ደ​ለም፤ ታማኝ እን​ድ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ያለኝ እንደ መሆኔ ምክ​ሬን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


የተ​ወ​ደደ ወን​ድ​ማ​ች​ንና የታ​መነ አገ​ል​ጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባ​ባ​ሪ​ያ​ችን የሆነ ቲኪ​ቆስ የእ​ኔን ዜና ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል።


ስለ​ዚ​ህም በየ​ስ​ፍ​ራው በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የሄ​ድ​ሁ​በ​ትን መን​ገድ ይገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መ​ነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን ልኬ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ለሠ​ራ​ተ​ኞ​ችም ይከ​ፍሉ ዘንድ ገን​ዘ​ቡን የሚ​ወ​ስ​ዱ​ትን ሰዎች አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር፤ በታ​ማ​ኝ​ነት ይሠሩ ነበ​ርና።


ነገር ግን እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ይሠሩ ነበ​ርና የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ገን​ዘብ አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር።


እኛ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ሥ​ጢሩ መጋ​ቢ​ዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እን​ዲህ ያስብ።


ለእ​ኔስ በእ​ና​ንተ ዘንድ መመ​ስ​ገን ውር​ደት ነው፤ ጻድቅ ብት​ሉኝ፥ በመ​ዋቲ ሰው ዘን​ድም ቸር ብላ​ችሁ ብታ​ከ​ብ​ሩኝ እኔ ለራሴ አል​ፈ​ር​ድም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios