Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዕቃ ቤቶ​ችም ላይ ካህ​ኑን ሰሌ​ም​ያን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳዶ​ቅን፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ፈዳ​ያን ሾምሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የመ​ታ​ንያ ልጅ የዘ​ኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነ​ር​ሱም የታ​መኑ ሆነው ተገኙ፤ ሥራ​ቸ​ውም ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ማከ​ፋ​ፈል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ለዕቃ ቤቶቹም ካህኑን ሰሌምያን፣ ጸሓፊውን ሳዶቅንና ፈዳያ የተባለውን ሌዋዊ ኀላፊ አድርጌ ሾምሁ፤ መደብሁ፤ እንዲሁም የመታንያን ልጅ፣ የዛኩርን ልጅ ሐናንን ረዳታቸው አደረግሁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ታማኞች ነበሩ። ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው የተመደበውን ቀለብ ማከፋፈል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም ፈዳያን ሾምሁ፥ ከእነርሱም ጋር የማታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፥ እነርሱም የታመኑ ሆነው ተገኙ፥ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለዕቃ ግምጃ ቤቱም ኀላፊነት ካህኑን ሼሌምያን፥ የሕግ ምሁሩን ሳዶቅንና ሌዋዊውን ፐዳያን መደብሁ፤ የማታንያ የልጅ ልጅ የሆነው የዛኩር ልጅ ሐናንም የእነርሱ ረዳት ነበር፤ እነዚህም ሰዎች ለሥራ ጓደኞቻቸው የሚሆነውን መተዳደሪያ ለማከፋፈል ታማኞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም ፈዳያን ሾምሁ፥ ከእነርሱም ጋር የመታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፥ እነርሱም የታመኑ ሆነው ተገኙ፥ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 13:13
20 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ሜን ሃና​ኒ​ንና የግ​ን​ቡን አለቃ ሐና​ን​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ሾም​ኋ​ቸው፤ እር​ሱም እው​ነ​ተኛ ከሌ​ሎ​ቹም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነበረ።


ነገር ግን እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ይሠሩ ነበ​ርና የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ገን​ዘብ አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር።


እን​ግ​ዲህ በዚህ ከመ​ጋ​ቢ​ዎች እያ​ን​ዳ​ንዱ ቸርና ታማኝ ሆኖ እን​ዲ​ገኝ ይፈ​ለ​ጋል።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን በመ​ል​ካም የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸ​ውን መን​ፈስ ቅዱ​ስና ጥበብ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ለዚህ ሥራም እን​ሾ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።


በዚ​ያም ወራት ደቀ መዛ​ሙ​ርት በበዙ ጊዜ ከግ​ሪክ የመጡ ደቀ መዛ​ሙ​ርት በአ​ይ​ሁድ ምእ​መ​ናን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​ባ​ቸው፤ የዕ​ለት የዕ​ለ​ቱን ምግብ ሲያ​ካ​ፍሉ ባል​ቴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቸል ይሉ​ባ​ቸው ነበ​ርና።


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።


ለሠ​ራ​ተ​ኞ​ችም ይከ​ፍሉ ዘንድ ገን​ዘ​ቡን የሚ​ወ​ስ​ዱ​ትን ሰዎች አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር፤ በታ​ማ​ኝ​ነት ይሠሩ ነበ​ርና።


እነዚህም ደግሞ አስቀድሞ ይፈተኑ፤ ከዚያም በኋላ ያለ ነቀፋ ቢሆኑ በዲቁና ሥራ ያገልግሉ።


ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኀይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤


አም​ጥ​ተ​ውም በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ፍላ​ጎቱ ይከ​ፍ​ሉት ነበር።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?


መለ​ከ​ትም ይዘው ከካ​ህ​ናቱ ልጆች አያ​ሌ​ዎች፥ የአ​ሳ​ፍም ልጅ የዘ​ኩር ልጅ የሚ​ካያ ልጅ የመ​ታ​ንያ ልጅ የሰ​ማ​ዕያ ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ዘካ​ር​ያስ፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥራ ላይ ከነ​በሩ መዘ​ም​ራን ከአ​ሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመ​ታ​ንያ ልጅ፥ የሐ​ሳ​ብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሌ​ዋ​ው​ያን አለቃ ነበረ።


ዘኩር፥ ሰራ​ብያ፥ ሰባ​ንያ፤


ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ሎ​ምያ ልጅ ሐና​ን​ያና የሴ​ሌፍ ስድ​ስ​ተ​ኛው ልጁ ሐኖን ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ። ከዚ​ያም በኋላ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ዐሥ​ራ​ቱን በተ​ቀ​በሉ ጊዜ የአ​ሮን ልጅ ካህኑ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋር ይሁን፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የዐ​ሥ​ራ​ቱን ዐሥ​ራት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ ጓዳ​ዎች ወደ ዕቃ ቤት ያም​ጡት።


ስለ በደ​ልና ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡት ገን​ዘ​ብም ለካ​ህ​ናት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios