ነህምያ 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቁም ካህን ኤልያሴብና ወንድሞቹ ካህናት ተነሥተው የበግ በር ሠሩ፤ ቀደሱትም፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፤ እስከ መቶ ግንብና እስከ ሐናንኤል ግንብ ድረስ ቀደሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናቱ ኤልያሴብና ወንድሞቹ ካህናት ለሥራ ተነሡ፤ የበጎች በር የተባለውንም እንደ ገና ሠሩ። ቀደሱት፤ መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ላይ አቆሙ። መቶ ግንብ እስከሚባለው ግንብና ሐናንኤል ግንብ ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ሠርተው ቀደሱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊቀ ካህኑ ኤልያሺብና ወንድሞቹ ካህናት ተነሥተው “የበግ በር” ሠሩ፤ ቀደሱት፥ በሩንም አቆሙ፤ እስከ “ሜአ ግንብ” እና እስከ “አሐናንኤል ግንብ” ድረስ ቀደሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቁም ካህን ኤልያሴብ ወንድሞቹም ካህናት ተነሥተው የበግ በር ሠሩ፥ ቀደሱትም፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ እስከ ሃሜአ ግንብና እስከ ሐናንኤል ግንብ ድረስ ቀደሱት። |
ከኤፍሬምም በር በላይ፥ በአሮጌው በርና በዓሣ በር፥ በአናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮዳሔ ልጆች አንዱ ለሐሮናዊው ለሰንባላጥ አማች ነበረ፤ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።
ከእርሱም በኋላ የዘቡር ልጅ ባሮክ ከማዕዘኑ ጀምሮ እስከ ታላቁ ካህን እስከ ኤልያሴብ ቤት መግቢያ ድረስ ሌላውን ክፍል ተግቶ ሠራ።
ከእርሱም በኋላ የአቆስ ልጅ የኡርያ ልጅ ሚራሞት ከኤልያሴብ ቤት መግቢያ ጀምሮ እሰከ ኤልያሴብ ቤት መጨረሻ ድረስ ሌላውን ክፍል ሠራ።
እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍራሹም አንዳች እንዳልቀረበት ሰንባላጥና ጦቢያ ዓረባዊውም ጌሳም የቀሩትም ጠላቶቻችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን አላቆምሁም ነበር።
“ከአናምሄል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን እነሆ ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ እንደ ዓረባ ትሆናለች፣ እርስዋም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው በር ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።
በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት።
ጸሐፍትም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመርቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።