Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እኔም መልሼ፥ “የሰ​ማይ አም​ላክ ያከ​ና​ው​ን​ል​ናል፤ እኛም ንጹ​ሓን ባሪ​ያ​ዎቹ ተነ​ሥ​ተን እን​ሠ​ራ​ለን፤ እና​ንተ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዕድል ፋን​ታና መብት፥ መታ​ሰ​ቢ​ያም የላ​ች​ሁም” አል​ኋ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እኔም፣ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛ ባሪያዎቹ እንደ ገና ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም ይገባናል የምትሉት ወይም የታሪክ መታሰቢያ የላችሁም” ስል መለስሁላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እኔም፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም አገልጋዮቹ እንነሳለን፥ እንሠራለንም፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም” ብዬ መለስኩላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔም “የሰማይ አምላክ ሥራችንን ለማከናወን ይረዳናል፤ እኛ የእርሱ አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ዐይነት ንብረት የማግኘት መብት ሆነ የታሪክ መታሰቢያነት አይኖራችሁም” ብዬ መለስኩላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እኔም መልሼ፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም አልኋቸው።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 2:20
21 Referencias Cruzadas  

በዚህ ነገር ዕድ​ልና ርስት የለ​ህም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብህ የቀና አይ​ደ​ለ​ምና።


ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ኢያ​ሱም፥ የቀ​ሩ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤል አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት መሥ​ራት ለእ​ኛና ለእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለም፤ እኛ ራሳ​ችን ግን የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዳ​ዘ​ዘን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ሠ​ራ​ለን” አሉ​አ​ቸው።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።


እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጸሎ​ትህ ተሰማ፤ ምጽ​ዋ​ት​ህም ታሰ​በ​ልህ።


በቤ​ቴና በቅ​ጥሬ ውስጥ ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች ይልቅ የሚ​በ​ልጥ ስም የሚ​ያ​ስ​ጠራ ቦታን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ይ​ጠፋ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ይህን ብት​ይዝ ለአ​ንተ መል​ካም ነው፤ በዚ​ህም እጅ​ህን አታ​ር​ክስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ከሁሉ ይወ​ጣ​ልና።


በማ​ዳ​ንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ጨመ​ር​ህ​ለት።


ወደ​እ​ር​ሱም ተመ​ል​ክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምን​ድን ነው?” አለ፤ መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ጸሎ​ት​ህም ምጽ​ዋ​ት​ህም መል​ካም መታ​ሰ​ቢያ ሆኖ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐር​ጎ​አል።


አክሊሎችም ለሔሌምና ለጦብያ ለዮዳኤም ለሶፎንያስም ልጅ ለሔን በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ ለመታሰቢያ ይሆናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ባስ​ተ​ማረ በዘ​ካ​ር​ያስ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ልብ አደ​ረገ፤ በዘ​መ​ኑም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነገ​ሩን አከ​ና​ወ​ነ​ለት።


ደግሞ በደ​ስ​ታ​ችሁ ቀን፥ በበ​ዓ​ላ​ታ​ች​ሁም ዘመን፥ በወ​ርም መባቻ፥ በሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁና በደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ላይ መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ እነ​ር​ሱም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


አሮ​ንም ወደ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስሞች በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸ​ከም።


በሁ​ለ​ቱም ተራ ንጹሕ ዕጣ​ንና ጨው ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ለተ​ዘ​ጋ​ጁት ኅብ​ስ​ቶች ይሁኑ።


ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመ​ጣ​ዋል፤ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄ​ቱና ከዘ​ይ​ቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩ​ንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ግን ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም በሚ​ፈ​ሩት ላይ፥ ጽድ​ቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios