Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 13:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከዋ​ነ​ኛ​ውም ካህን ከኤ​ል​ያ​ሴብ ልጅ ከዮ​ዳሔ ልጆች አንዱ ለሐ​ሮ​ና​ዊው ለሰ​ን​ባ​ላጥ አማች ነበረ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አባ​ረ​ር​ሁት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ የሖሮናዊው የሰንባላጥ አማች ነበረ፤ እኔም ከአጠገቤ አባረርሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ ልጆች አንዱ ዮያዳዕ ነበር፤ ነገር ግን ከእርሱ ልጆች አንዱ የቤትሖሮን ከተማ ነዋሪ የሆነውን የሰንባላጥን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፤ ስለዚህም ዮያዳዕ ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲወጣ አደረግሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 13:28
14 Referencias Cruzadas  

“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማ​ይ​መጣ ሁሉ እንደ ሽማ​ግ​ሎ​ችና እን​ዳ​ለ​ቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበ​ዝ​በዝ፤ እር​ሱም ከም​ር​ኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ።


ኢያ​ሱም ዮአ​ቂ​ምን ወለደ፤ ዮአ​ቂ​ምም ኤሊ​ያ​ሴ​ብን ወለደ፤ ኤሊ​ያ​ሴ​ብም ዮሐ​ዳን ወለደ፤


ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በኤ​ል​ያ​ሴ​ብና በዮ​ሐዳ፥ በዮ​ሐ​ና​ንና በያ​ዱዕ ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ተጻፉ፤ ካህ​ና​ቱም በፋ​ር​ሳ​ዊው በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት ዘመን ተጻፉ።


እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።


ታላ​ቁም ካህን ኤል​ያ​ሴ​ብና ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናት ተነ​ሥ​ተው የበግ በር ሠሩ፤ ቀደ​ሱ​ትም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ እስከ መቶ ግን​ብና እስከ ሐና​ን​ኤል ግንብ ድረስ ቀደ​ሱት።


ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው።


ጠላ​ቶቼ ሁል​ጊዜ ይሰ​ድ​ቡ​ኛል፥ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም ተማ​ማ​ሉ​ብኝ።


ብልህ ንጉሥ የኃጥኣን መንሽ ነው፥ በእነርሱ ላይም መንኰራኵርን ይነዳባቸዋል።


እውነተኛ ንጉሥ በዙፋኑ በተቀመጠ ጊዜ በዐይኖቹ ፊት ምንም ክፉ አይቃወመውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos