የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
ነህምያ 12:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ጊዜ ለቤተ መቅደስ መገልገያ የሚደረገውን አስተዋጽዖ እንዲሁም ከዐሥር አንዱን፥ በየዓመቱ በመጀመሪያ የሚደርሰውን እህልና ፍራፍሬ በማከማቸት የዕቃ ቤት ክፍሎችን የሚጠብቁ ኀላፊዎች ተሾሙ፤ እነዚህም ሰዎች በልዩ ልዩ ከተሞች አቅራቢያ ከሚገኙ የእርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የተመደበውን አስተዋጽዖ የመሰብሰብ ኀላፊነት ነበራቸው፤ የይሁዳም ሕዝብ በሙሉ በካህናቱና በሌዋውያኑ እጅግ ደስ ብሎአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኩራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ። |
የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር።
እነዚህ አራቱ ኀያላን ሰዎች ለአራቱ በሮች ኀላፊዎች ነበሩ። ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ የተሾሙ ነበሩ።
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
አሮንንና ልጆቹን በምስክሩ ድንኳን ፊት አቁማቸው፤ ክህነታቸውንም፥ በመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያለውንም ሁሉ ይጠብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።”