Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 12:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 እነ​ር​ሱም መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ሥር​ዐት የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውን ሥር​ዐት እንደ ዳዊ​ትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎ​ሞን ትእ​ዛዝ ጠበቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 የይሁዳም ሕዝብ ተደስቶ የነበረው እነርሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መፈጸም የሚገባውን ደንብና የማንጻት ሥርዓት በማከናወናቸው ነበር፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራንና የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎችም ዳዊትና ልጁ ሰሎሞን በመደቡት ሥርዓት መሠረት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ፈጸሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 12:45
5 Referencias Cruzadas  

ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው በር ጮኹ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፥ “ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ገባን፤ እነ​ሆም፥ ፈረ​ሶ​ችና አህ​ዮች ታስ​ረው፥ ድን​ኳ​ኖ​ችም ተተ​ክ​ለው ነበር እንጂ ያገ​ኘ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ውም ድምፅ አል​ነ​በ​ረም።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ይህ ሰሎ​ሚ​ትና ወን​ድ​ሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊ​ትና የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች፥ በቀ​ደ​ሱት በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ላይ ተሹ​መው ነበር።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ግን ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አገ​ል​ጋ​ዮች በቀር ማንም አይ​ግባ፤ እነ​ርሱ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ይግቡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቅ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos