ነህምያ 12:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመዘምራኑም ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙርያና ከሌሎችም መንደሮች ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ተሰበሰቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም በዓል ለማክበር የሌዋውያኑ ቤተሰቦች መዘምራን ሁሉ ሰፍረው ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም አካባቢና በነጦፋ ከሚገኙት ታናናሽ ከተሞች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። |
ለሌዋውያንም ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄደ ተመለከትሁ።
ሰንባላጥና ጌሳም፥ “መጥተህ በኦኖ ቈላ ውስጥ ባሉት መንደሮች እንገናኝ” ብለው ላኩብኝ፤ ነገር ግን ክፉ ያደርጉብኝ ዘንድ ይመክሩ ነበር።