Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ፈን​ታ​ቸው እን​ዳ​ል​ተ​ሰጠ፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሌዋ​ው​ያ​ንና መዘ​ም​ራን እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ እር​ሻው እንደ ሄደ ተመ​ለ​ከ​ትሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲሁም ለሌዋውያን የተመደበው ድርሻ እንዳልተሰጣቸውና አገልግሎቱን በኀላፊነት የሚመሩ ሌዋውያንና መዘምራን ሁሉ ወደየርስታቸው መመለሳቸውን ተረዳሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለሌዋውያንም እድል ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄዱ ተመለከትሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንዲሁም አገልግሎቱን የሚፈጽሙት የቤተ መቅደሱ መዘምራንና ሌሎችም ሌዋውያን ኢየሩሳሌምን ለቀው በመውጣት ወደየእርሻቸው ተመልሰው መግባታቸውን ተገነዘብኩ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሕዝቡ ለመዘምራኑና ለሌዋውያኑ በቂ መተዳደሪያ ባለመስጠታቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለሌዋውያንም እድል ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄዱ ተመለከትሁ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 13:10
11 Referencias Cruzadas  

የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን።


ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና በነ​ህ​ምያ ዘመን ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑና ለበ​ረ​ኞቹ ፈን​ታ​ቸ​ውን በየ​ዕ​ለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ነገር ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር ለአ​ሮን ልጆች ሰጡ።


በም​ድ​ርህ ላይ በም​ት​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ ሌዋ​ዊ​ዉን ቸል እን​ዳ​ትል ተጠ​ን​ቀቅ።


“ሌዋ​ው​ያን የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞች ከሚ​ካ​ፈ​ሉት ርስ​ታ​ቸው ይሰጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው፤ በከ​ተ​ሞ​ቹም ዙሪያ ያሉ​ትን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ለሌ​ዋ​ው​ያን ይስ​ጡ​አ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የሌዊ ልጆ​ችም የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ​ዎ​ችና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራኑ ወዳ​ሉ​ባ​ቸው ጓዳ​ዎች ያግ​ቡት፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት ከቶ አን​ተ​ውም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ጸኑ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያን ድር​ሻ​ቸ​ውን ይሰጡ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሕዝብ አዘዘ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በጎ​ች​ህን አላ​ቀ​ረ​ብ​ህ​ል​ኝም፤ በሌ​ላም በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትህ አላ​ከ​በ​ር​ኸ​ኝም፤ በእ​ህ​ልም ቍር​ባን አላ​ስ​ቸ​ገ​ር​ሁ​ህም፤ በዕ​ጣ​ንም አላ​ደ​ከ​ም​ሁ​ህም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios