ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ሰጡ፤ የሁሉንም ዐሥራት አብዝተው አቀረቡ።
ነህምያ 10:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲሁም በሕጉ እንደ ተጻፈው የወንድ ልጆቻችንንና፣ የቀንድ ከብቶቻችንን፣ የመንጋዎቻችንን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችንን በኵራት ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደሚያገለግሉትም ካህናት እናመጣለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኩራት፥ የበሬዎችቻችንንና የበጎቻችንን በኩራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ የእህላችንንም በኩራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። |
ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ሰጡ፤ የሁሉንም ዐሥራት አብዝተው አቀረቡ።
የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ።
ለሌዋውያን፥ ለመዘምራንና ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ዐሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን ቀዳምያቱን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘጋጅቶለት ነበር።
“በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም፥ ከእንስሳም መጀመሪያ የተወለደውን ማሕፀንን የሚከፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይልኝ፤ የእኔ ነው።”
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይችአለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ቀዳምያታችሁን፥ ስዕለታችሁንም፥ በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኵራት ውሰዱ።