Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


ነህምያ 10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ያተሙትም የሐካልያ ልጅ የሆነው አገረ ገዢው ነህምያ፥ ሴዴቅያስ።

2-8 ከካህናት ወገን፦ ሠራያ፥ ዐዛርያ፥ ኤርምያስ፥ ፓሽሑር፥ አማርያ፥ ማልኪያ፥ ሐጡሽ፥ ሸባንያ፥ ማሉክ፥ ሐሪም፥ መሬሞት፥ አብድዩ፥ ዳንኤል፥ ጊነቶን፥ ባሩክ፥ መሹላም፥ አቢያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቢልጋይና ሸማዕያ።

9-13 ከሌዋውያን ወገን፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥ ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ።

14-27 ከሕዝቡ መሪዎች ወገን፦ ፓርዖሽ፥ ፓሐትሞአብ፥ ዔላም፥ ዛቱ፥ ባኒ፥ ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥ አዶኒያ፥ ቢግዋይ፥ ዓዲን፥ አጤር፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዙር፥ ሆዲያ፥ ሐሹም፥ ቤጻይ፥ ሐሪፍ፥ ዐናቶት፥ ኔባይ፥ ማግፒዓሽ፥ መሹላም፥ ሔዚር፥ መሼዛብኤል፥ ጻዶቅ፥ ያዱዐ፥ ፐላጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፥ ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ ሐሹብ፥ ሀሎሔሽ፥ ፒልሐ፥ ሾቤቅ፥ ረሑም፥ ሐሻብና፥ ማዕሤያ፥ አኪያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥ ማሉክ፥ ሐሪምና በዓና።


የተደረገው ስምምነት

28 የቀሩትም ሰዎች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራን፥ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና ለእግዚአብሔር ሕግ ታዛዦች የሆኑ በጐረቤት ከሚኖሩት የባዕዳን አገር ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ፥ ከሚስቶቻቸው፥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው ጋር፥

29 እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።

30 በአካባቢአችን ላሉት አሕዛብ ሴቶች ልጆቻችንን በጋብቻ እንደማንሰጥና ወይም የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን በጋብቻ እንደማንወስድ ቃል እንገባለን።

31 የባዕዳን አገር ሕዝቦች በሰንበት ቀን ወይም በሌሎች በዓላት እህልም ሆነ ሌላ የንግድ ሸቀጥ ይዘው ቢመጡ፥ ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ምድሪቱን አናርስም፤ ያበደርነውንም ዕዳ ሁሉ እንሰርዛለን።

32 በየዓመቱ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውል እያንዳንዳችን የጥሬ ብር አንድ ሦስተኛ እጅ በማምጣት እንሰጣለን።

33 እንዲሁም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ከዚህ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልተን እናቀርባለን፦ ይኸውም የተቀደሰውን ኅብስት፥ በየዕለቱ መቅረብ የሚገባውን የእህል መባ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑትን እንስሶች፥ በሰንበት ቀኖች፥ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ጊዜና በሌሎችም በዓላት የሚቀርበውን፥ ሌላውንም የተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ ኃጢአት ማስተስረያ መቅረብ የሚገባውንና ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ሌላውንም ነገር ሁሉ አናስታጒልም።

34 በሕጉ ስለ መሥዋዕት በተጻፈው መሠረት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መሥዋዕት የሚቃጠልበትን የማገዶ እንጨት የትኞቹ ጐሣዎች ማቅረብ እንደሚገባቸው እኛ ሕዝቡ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ በየዓመቱ ዕጣ በማውጣት እንወስናለን።

35 የእህላችንን መከር በምንሰበስብበት ወቅትና የዛፎቻችንን ፍሬ በምንለቅምበት ወራት በመጀመሪያ የደረሰውን እሸት፥ ወደ ቤተ መቅደስ እያመጣን እናበረክታለን።

36 ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን።

37 ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን።

38 ዐሥራቱም በሚሰበሰብበት ጊዜ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆኑ ካህናት፥ ከሌዋውያኑ ጋር ይገኛሉ፤ ለቤተ መቅደሱም አገልግሎት ሌዋውያኑ ከሚሰበስቡት ዐሥራት ውስጥ እንደገና ከዐሥር አንዱን አወጣጥተው ወደ ቤተ መቅደሱ የዕቃ ግምጃ ቤት ያስገባሉ።

39 የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ የእህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት ስጦታዎችን ይዘው ንዋያተ ቅዱሳት ወደሚቀመጡበትና አገልጋዮቹ ካህናት፥ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉበት ዕቃ ግምጃ ቤት ማምጣት አለባቸው። የእግዚአብሔርን ቤት ከቶ ቸል አንልም።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos