ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር።
ናሆም 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች። ልብ ቀልጧል፤ ጕልበት ተብረክርኳል፤ ሰውነት ተንቀጥቅጧል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ፤ ሃብቷ ማለቂያ የለውምና፥ የከበረው የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቆጠርምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነነዌ ተደመሰሰች፤ ፈራርሳም ወደመች፤ የሰው ልብ በፍርሃት ቀለጠ፤ ጉልበቶችም ተብረከረኩ፤ የሰው ሁሉ ወገብ ተንቀጠቀጠ። የሰውም ሁሉ ፊት ገረጣ፤ |
ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር።
“ባቢሎንን የወፎች መኖሪያ አደርጋታለሁ፤ እንደ ኢምንትም ትሆናለች፤ በጥፋትም እንደ ረግረግ ጭቃ አደርጋታለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕማሜ የተነሣ አልሰማም፤ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ዓለምን ያጠፋታል፤ ባድማም ያደርጋታል፤ ይገለብጣትማል፤ በእርስዋም የተቀመጡትን ይበትናል።
ጠይቁ፤ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍረት ተለውጦ አየሁ?
“ስለ ደማስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ፤ ቀለጡም፤ እንደ ባሕርም ተነዋወጡ፤ ያርፉም ዘንድ አይችሉም።
አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተናግረሃል በል።
በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ወድቄ ተሰብሬአለሁ፤ ጠቍሬማለሁ፤ ራስ ማዞርም ይዞኛል፤ ምጥ እንደያዛትም ሴት በመከራው እጨነቃለሁ።
እነርሱም፦ ስለ ምን ታለቅሳለህ? ቢሉህ አንተ እንዲህ በላቸው፦ ስለሚመጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀልጣል፤ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፤ ሥጋና መንፈስ ሁሉ ይደክማል፤ ከጕልበትም እዥ ይፈስሳል፤ እነሆ ይመጣል፤ ይፈጸማልም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶን አስለቀስሁ፤ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት፤ ፈሳሾችንም ከለከልሁ፤ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት። የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።
አሕዛብን አጥፍቻለሁ፣ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፣ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።
ይህንም ነገር ሰምተን በልባችን ደነገጥን፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእኛ የአንዱም እንኳን ነፍስ አልቀረም።
የጋይ ሰዎችም ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀምረው እስከ አጠፉአቸው ድረስ አባረሩአቸው፤ በቍልቍለቱም ገደሉአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ደነገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።