Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ናሆም 2:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነነዌ ተደመሰሰች፤ ፈራርሳም ወደመች፤ የሰው ልብ በፍርሃት ቀለጠ፤ ጉልበቶችም ተብረከረኩ፤ የሰው ሁሉ ወገብ ተንቀጠቀጠ። የሰውም ሁሉ ፊት ገረጣ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች። ልብ ቀልጧል፤ ጕልበት ተብረክርኳል፤ ሰውነት ተንቀጥቅጧል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቷል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ፤ ሃብቷ ማለቂያ የለውምና፥ የከበረው የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቆጠርምና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 2:10
24 Referencias Cruzadas  

ጒልበቴ ደክሞ እንደ ውሃ ፈሰሰ፤ አጥንቶቼ ሁሉ ከመገጣጠሚያቸው ተለያዩ፤ ልቤም እንደ ሰም በውስጤ ቀለጠ።


እነርሱን በሚያዩበት ጊዜ ሕዝቦች ይርበደበዳሉ፤ የሰውም ሁሉ ፊት በፍርሃት ይገረጣል።


ወዲያውኑ ፊቱ ገረጣ፤ ከድንጋጤውም ብዛት የተነሣ ጒልበቱ ተብረከረከ፤ የሰውነቱ መገጣጠሚያዎች ከዱት።


እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ! ወንድ አምጦ ልጅን መውለድ ይችላልን? ታዲያ ወንድ ሁሉ እንደ ወላድ ሴት በእጆቹ ወገቡን ይዞ የማየው ስለምንድን ነው? የእያንዳንዱስ ሰው ፊት ስለምን ገረጣ?


እነሆ እግዚአብሔር ምድሪቱን አፈራርሶ ባድማ ያደርጋታል፤ የዚያችንም ምድር ገጽታ ለዋውጦ ሕዝቦችዋን ይበትናል፤


በዚህም ምክንያት ሰውነቴ ታመመ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴትም አስጨነቀኝ፤ በምሰማው ነገር ታወክሁ፤ በማየውም ነገር ግራ ተጋባሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብ “መንግሥታትን አጠፋሁ፤ ምሽጎቻቸውን አፈራረስኩ፤ መንገዶቻቸውን ማንም የማይተላለፍባቸው ባዶ አድርጌአቸዋለሁ፤ ከተሞቻቸውን ሕዝብ የሌለባቸው፥ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አድርጌአቸዋለሁ።


የሚያይሽ ሁሉ በመሸማቀቅ ‘እነሆ ነነዌ ፈራርሳ ውድማ ሆናለች፤ ማን ያዝንላታል?’ ይላል። የሚያጽናናትስ እኔ ከወዴት አገኝላታለሁ?”


ከዚያም በኋላ ‘ጌታ ሆይ! አንተ ይህን ስፍራ እንደምታጠፋ ተናግረሃል፤ ስለዚህም ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ፍጥረት አይኖርባትም፤ ሰውም እንስሳም ስለሚጠፋ ለዘለዓለም ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች’ በል።


ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


ስለዚህም ይህን ሁሉ ነገር በሰማን ጊዜ በፍርሃት ልባችን ቀለጠ፤ ወኔአችን ሁሉ ጠፋ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእርግጥ የሰማይና የምድር አምላክ ነው።


በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።


የዐይ ሰዎችም ወደ ሠላሳ ስድስት ያኽል ሰዎችን ገደሉባቸው፤ ከከተማይቱ ቅጥር በር ጀምሮ እስከ ሼባሪዎ ቊልቊለት ድረስ እየገደሉ አባረሩአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀልጦ እንደ ውሃ ፈሰሰ።


ሕዝቤ በመሰበሩ የእኔም ልብ ተሰብሮአል፤ ፍርሀትም ይዞኝ አለቅሳለሁ።


“የሐማትና የአርፋድ ከተማ ነዋሪዎች የደማስቆን የጥፋት ወሬ ስለ ሰሙ ግራ ተጋቡ፤ ወደ ላይና ወደ ታች እንደሚናወጥ ባሕር የእነርሱም ልብ ተሸበረ።


“ለምን ትቃትታለህ” ብለው ቢጠይቁህ “ስለሚመጣው ወሬ ነው” ትላቸዋለህ፤ “በዚያም ወሬ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ወኔ ሁሉ ይከዳል፤ ጒልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ እነሆ እየመጣ ነው፤ በእርግጥ ይፈጸማል” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ያ ዛፍ ተቈርጦ ወደ ሙታን ዓለም በሚወርድበት ጊዜ ጥልቁን ውሃ ዘግቼ እየተለቀሰለት ይሸፈናል። ወንዞችም እንዲቋረጡ አደርጋለሁ፤ ኀይለኞቹ ወራጅ ውሃዎችም እንዲቆሙ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት በሊባኖስ ተራራዎች ላይ የጨለማ ግርዶሽ አመጣለሁ፤ ስለዚህም የሜዳ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ።


አጥፊዎች እነርሱንና ሀብታቸውን ቢያወድሙም እንኳ እግዚአብሔር የያዕቆብ ልጆች የሆኑትን የእስራኤልን ክብር ይመልሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios