ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
ማቴዎስ 27:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዘውትም ሲሄዱ ስምዖን ተብሎ የሚጠራ የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉንም እንዲሸከም አስገደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲወጡም ስምዖን የሚባል የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉንም እንዲሸከም አስገደዱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከገዢው ግቢ ሲወጡ ሳሉ ስምዖን የተባለውን የቀሬና አገር ሰው አገኙና የኢየሱስን መስቀል እንዲሸከም አስገደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት። |
ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
እነሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እንግዲህ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው።
ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደሚፈስስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዱታል፤ በዕንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥሉታል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።
ወይፈኑንም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ይወስዱታል፤ የፊተኛውንም ወይፈን እንዳቃጠሉ ያቃጥሉታል፤ የማኅበሩ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።
በወሰዱትም ጊዜ የቀሬና ሰው ስምዖንን ከዱር ሲመለስ ያዙት፤ ከጌታችን ከኢየሱስም በስተኋላ መስቀሉን አሸከሙት።
ከመካከላቸውም ወደ አንጾኪያ ሄደው ለአረማውያን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ነገር ያስተማሩ የቆጵሮስና የቄሬና ሰዎች ነበሩ።
በአንጾኪያ በነበረችው ቤተ ክርስቲያንም ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖን፥ የቀሬናው ሉቅዮስ፥ ከአራተኛው ክፍል ገዢ ከሄሮድስ ጋር ያደገው ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።
የነጻ ወጭዎች ከምትባለው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያ፥ ከቂልቅያና ከእስያ የሆኑ ሰዎችም ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር።
ከከተማም ወደ ውጭ ጐትተው አውጥተው ወገሩት፤ የሚወግሩት ሰዎችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል ጐልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።