Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲሁም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና፣ ‘እግዚአብሔርንም ንጉሡንም ሰድቧል’ ብለው ይመስክሩበት፤ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ‘እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል’ ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያም በኋላ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወልደ አዴርም፦ ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደ ሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ ብሎ ላከበት።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 21:10
18 Referencias Cruzadas  

“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


ከዚ​ህም በኋላ “ይህን ሰው በሙ​ሴና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የስ​ድ​ብን ቃል ሲና​ገር ሰም​ተ​ነ​ዋል” የሚሉ የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ችን አስ​ነ​ሡ​በት፤


“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማ​ድ​ረ​ግም ስለ​ሚ​ሠ​ራት ኀጢ​አት ሁሉ በማ​ንም ላይ አንድ ምስ​ክር አይ​ሁን፤ በሁ​ለት ምስ​ክ​ሮች ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸ​ናል።


ክፋ​ተ​ኞች ሰዎች ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወጥ​ተው፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብለው የከ​ተ​ማ​ቸ​ውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብት​ሰማ፥


የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ሙ​በት፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅ​ደስ ላይና በኦ​ሪት ላይ የስ​ድብ ቃል እየ​ተ​ና​ገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ፥ ሰው ስት​ሆን ራስ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህና፤ ስለ መሳ​ደ​ብህ ነው እንጂ ስለ መል​ካም ሥራ​ህስ አን​ወ​ግ​ር​ህም” አሉት።


ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች የሆኑ የከ​ተ​ማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩ​ንም ይደ​በ​ድቡ ነበር፤ ባለ​ቤ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገ​ባ​ውን ሰው እን​ድ​ን​ደ​ር​ስ​በት አው​ጣ​ልን” አሉት።


“ተሳ​ዳ​ቢ​ውን ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አው​ጣው፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን በራሱ ላይ ይጫ​ኑ​በት፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።”


የካ​ህ​ኑም የዔሊ ልጆች ክፉ​ዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አያ​ው​ቁም ነበር።


በዚ​ያም አንድ ብን​ያ​ማዊ የቢ​ኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚ​ባል የዐ​መፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ከዳ​ዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለ​ንም፦ ከእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድህ ወደ ድን​ኳ​ንህ ተመ​ለስ” ብሎ መለ​ከት ነፋ።


ለወ​ልደ አዴር መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችሁ፦ ለእኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በመ​ጀ​መ​ሪያ የላ​ክ​ህ​ብ​ኝን ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ይህን ነገር ግን አደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም” በሉት አላ​ቸው። መል​ክ​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ተመ​ል​ሰው ይህን ነገር ነገ​ሩት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መልሶ፥ “ይሁን፤ ይህ ጐባጣ እንደ ቀና አይ​መካ” ብሎ መለሰ።


ኤል​ሳዕ ግን በቤቱ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ንጉ​ሡም በፊቱ ከሚ​ቆ​ሙት አንድ ሰው ላከ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ገና ሳይ​ደ​ርስ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ይህ የነ​ፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን ይቈ​ርጥ ዘንድ እንደ ላከ እዩ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም በመጣ ጊዜ ደጁን ዘግ​ታ​ችሁ ከል​ክ​ሉት፤ በደ​ጅም ይቆም ዘንድ ተዉት፤ የጌ​ታው የእ​ግሩ ኮቴ በኋ​ላው ነው” አላ​ቸው።


የግ​ብ​ዣ​ውም ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይል​ክና ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ነበር፤ በማ​ለ​ዳም ገሥ​ግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍ​ጥ​ራ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ አንድ ወይ​ፈን ስለ ነፍ​ሳ​ቸው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምና​ል​ባት ልጆቼ በል​ባ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆ​ናል” ይል ነበ​ርና።


ሐሰተኛ ምስክርን የሚያቀጣጥል፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።


ፍር​ድን ከመ​ከ​ተል ወደ ኋላ ርቀ​ናል፤ ጽድ​ቅም በሩቅ ቆሞ​አል፤ እው​ነ​ትም ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ታጥ​ቶ​አል፤ በቀና መን​ገ​ድም መሄድ አል​ቻ​ሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios