እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
ሚልክያስ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ ወድጃችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት ወደድኸን?’ ትላላችሁ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ያዕቆብን ወደድሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሕዝቡን “እኔ እናንተን ወድጄአችኋለሁ” ይላል። እናንተ ግን “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፥ “ዔሳውና ያዕቆብ ወንድማማቾች ነበሩ፤ እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ፥ |
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ፤ እንዲህም አለ፥ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣው ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረክሁትም፤ እርሱም የተባረከ ነው።”
እንዲህም አለኝ፦ እነሆ፥ አበዛሃለሁ፤ አባዛሃለሁም፤ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለዘለዓለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
በፊቴ የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ብዙ ሰዎችን ለአንተ ቤዛ፥ አለቆችንም ለራስህ እሰጣለሁ።
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ አንገዛልህም፤ ከእንግዲህም ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?
እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “በዘለዓለም ፍቅር ወድጄሃለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁህ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦“ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ በምድር ላይም ማኅፀንን አርክሶአልና፥ የሚዘልፈውንና የሚያስደነግጠውን በርብሮአልና፥ መዓቱንም ለዘለዓለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤዶምያስ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።
ብቻ እግዚአብሔር አባቶቻችሁን መረጣቸው፤ ወደዳቸውም፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መረጠ።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በለዓምን ይሰማ ዘንድ አልወደደም፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ወድዶሃልና ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠልህ።