La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንድ የመቶ አለ​ቃም ነበረ፤ አገ​ል​ጋ​ዩም ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር፤ እር​ሱም በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያም አንድ የመቶ አለቃ ነበረ፤ እጅግ የሚወድደው ባሪያውም ታምሞበት ለሞት ተቃርቦ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድ የመቶ አለቃም ነበረ፤ የሚወደውም ባርያው ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም አንድ ሮማዊ የመቶ አለቃ ነበረ። እርሱም የሚወድደው አገልጋይ በጠና ታሞበት ለሞት ተቃርቦ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንድ የመቶ አለቃም ነበረ፤ የሚወደውም ባሪያው ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር።

Ver Capítulo



ሉቃስ 7:2
24 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “ቸር​ነ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ከጌ​ታዬ ያላ​ራቀ የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ለእ​ኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብ​ር​ሃም ወን​ድም ቤት መን​ገ​ዴን አቀ​ና​ልኝ።”


የር​ብቃ ሞግ​ዚት ዲቦ​ራም ሞተች፤ ከቤ​ቴል በታች ባላን በሚ​ባል ዛፍ ሥርም ተቀ​በ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ስሙን “የል​ቅሶ ዛፍ” ብሎ ጠራው።


ከፌ​ዘ​ኞች ጋር ሄጄ እንደ ሆነ፥ እግ​ሬም ከመ​ን​ገዱ ገለል ብላ እንደ ሆነ፥


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


የመቶ አለ​ቃ​ውም የሆ​ነ​ውን ነገር አይቶ፥ “ይህ ሰው በእ​ው​ነት ጻድቅ ነበረ”ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው።


ለሕ​ዝ​ቡም ቃሉን ነግሮ ከፈ​ጸመ በኋላ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ገባ።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ አገ​ል​ጋ​ዩን እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ለት ይማ​ል​ዱት ዘንድ የአ​ይ​ሁ​ድን ሽማ​ግ​ሎች ወደ እርሱ ላከ።


ዕድ​ሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚ​ሆ​ናት አን​ዲት ልጅ ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም ልት​ሞት ቀርባ ነበ​ረች።


በቂ​ሳ​ር​ያም ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢጣ​ሊቄ ለሚ​ሉት ጭፍ​ራም የመቶ አለቃ ነበር።


ያነ​ጋ​ገ​ረ​ውም መል​አክ ከሄደ በኋላ ከሎ​ሌ​ዎቹ ሁለት፥ ከማ​ይ​ለ​ዩት ጭፍ​ሮ​ቹም አንድ ደግ ወታ​ደር ጠራ።


የመቶ አለ​ቃ​ውም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ሻለ​ቃው ሄደና፥ “ይህ ሰው ሮማዊ ነው፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ዕወቅ” ብሎ ነገ​ረው።


ጳው​ሎ​ስም ከመቶ አለ​ቆች አን​ዱን ጠርቶ፥ “የሚ​ነ​ግ​ረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻ​ለ​ቃው አድ​ር​ስ​ልኝ” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሲዶና ደረ​ስን፤ ዩል​ዮ​ስም ለጳ​ው​ሎስ አዘ​ነ​ለት፤ ወደ ወዳ​ጆቹ እን​ዲ​ሄ​ድና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ር​ፍም ፈቀ​ደ​ለት።


የመቶ አለ​ቃው ግን ጳው​ሎ​ስን ሊያ​ድ​ነው ወድ​ዶ​አ​ልና ምክ​ራ​ቸ​ውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ዋኝ​ተው ወደ ምድር እን​ዲ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።


አገ​ል​ጋ​ዮች ሆይ በቅን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ም​ታ​ሰኙ ለታ​ይታ የም​ት​ገዙ ሳት​ሆኑ፥ በሥጋ ጌቶ​ቻ​ችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።