Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 8:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ዕድ​ሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚ​ሆ​ናት አን​ዲት ልጅ ነበ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም ልት​ሞት ቀርባ ነበ​ረች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ይህን ልመና ያቀረበው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆነ አንዲት ልጅ ስለ ነበረችው ነው፤ እርሷ በሞት አፋፍ ላይ ነበረች። ወደዚያው እያመራ ሳለ፣ ሕዝቡ በመጋፋት እጅግ ያጨናንቀው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርሷም ለመሞት እያጣጣረች ነበር። ሲሄድም ሕዝቡ በዙርያው እየተጋፉት ያጨናንቁት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ይህንንም ያለው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንድያ ልጁ ታማ በሞት አፋፍ ላይ ስለ ነበረች ነው። ኢየሱስም ከእርሱ ጋር አብሮ ሲሄድ ሳለ ተከትለውት የነበሩ ብዙ ሰዎች በመጨናነቅ ይጋፉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 አሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርስዋም ለሞት ቀርባ ነበረች። ሲሄድም ሕዝቡ ያጨናንቁት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 8:42
15 Referencias Cruzadas  

ከጥ​ዋት እስከ ማታ አይ​ኖ​ሩም። ራሳ​ቸ​ውን ማዳ​ንና መር​ዳት አይ​ች​ሉ​ምና ጠፉ።


ሰው በከ​ንቱ ወራቱ ቍጥ​ርና እንደ ጥላ በሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ዘመኑ በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ለሰው የሚ​ሻ​ለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?


“የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐ​ይ​ን​ህን አም​ሮት በመ​ቅ​ሠ​ፍት እወ​ስ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ዋይ አት​በል፤ አታ​ል​ቅ​ስም፤ እን​ባ​ህ​ንም አታ​ፍ​ስስ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይ​ላ​ቸ​ውን፥ የተ​መ​ኩ​በ​ት​ንም ደስታ፥ የዐ​ይ​ና​ቸ​ው​ንም አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ምኞት፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ሰ​ድ​ሁ​ባ​ቸው ቀን፥


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።


ወደ ከተ​ማው በር በደ​ረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያን​ዲት መበ​ለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳ​ውን ተሸ​ክ​መው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸ​ውም ለእ​ናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙ​ዎ​ችም የከ​ተማ ሰዎች አብ​ረ​ዋት ነበሩ።


እነ​ሆም ኢያ​ኢ​ሮስ የሚ​ባል ሰው መጣ፤ እር​ሱም የም​ኵ​ራብ ሹም ነበር፤ ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር በታ​ችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመ​ነው።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማን ዳሰ​ሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሰው ይጋ​ፋ​ህና ያጨ​ና​ን​ቅህ የለ​ምን? አንተ ግን ማን ዳሰ​ሰኝ? ትላ​ለህ” አሉት።


ስለ​ዚ​ህም በአ​ንድ ሰው በደል ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለ​ዚ​ችም ኀጢ​አት ሞት ገባ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ ኀጢ​አ​ትን ስለ አደ​ረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos