Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ያነ​ጋ​ገ​ረ​ውም መል​አክ ከሄደ በኋላ ከሎ​ሌ​ዎቹ ሁለት፥ ከማ​ይ​ለ​ዩት ጭፍ​ሮ​ቹም አንድ ደግ ወታ​ደር ጠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ቆርኔሌዎስም፣ ያነጋገረው መልአክ ተለይቶት ከሄደ በኋላ፣ ከአገልጋዮቹ ሁለቱን፣ እንዲሁም በመንፈሳዊ ነገር የተጋና ለርሱ ታማኝ የሆነውን አንዱን ወታደር አስጠራ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህን የነገረው መልአክ ተለይቶት በሄደ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ከአገልጋዮቹ ሁለቱንና የእርሱ ክፍል ከሆኑት ወታደሮች እግዚአብሔርን የሚፈራውን አንዱን ጠራና፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሎዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 10:7
13 Referencias Cruzadas  

ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?


ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው፥ “እኛሳ ምን እና​ድ​ርግ?” አሉት፤ “በደ​መ​ወ​ዛ​ችሁ ኑሩ እንጂ በማ​ንም ግፍ አት​ሥሩ፤ ማን​ንም አት​ቀሙ፤ አት​በ​ድ​ሉም” አላ​ቸው።


ብቻ​ህ​ንም ለመ​ው​ረድ ብት​ፈራ አንተ ከሎ​ሌህ ፋራን ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤


የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።


የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ ነገ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።


እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ” አለው።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስሙ ስም​ዖን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ጻድ​ቅና ደግ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ደስ​ታ​ቸ​ውን ያይ ዘንድ ተስፋ ያደ​ርግ ነበር፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስም ያደ​ረ​በት ነበር።


እር​ሱም ቤቱ በባ​ሕር አጠ​ገብ ባለው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት እን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ም​ጦ​አል። ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን እርሱ ይነ​ግ​ር​ሃል።”


ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ነግሮ ወደ ኢዮጴ ከተማ ላካ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios