ሉቃስ 12:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴንም፣ “ነፍሴ ሆይ፤ ለብዙ ዘመን የሚበቃሽ ሀብት አከማችቼልሻለሁ፤ እንግዲህ ዕረፊ፤ ብዪ፤ ጠጪ፤ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴንም አንቺ ነፍሴ! ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፤ ብዪ፤ ጠጪ፤ ደስ ይበልሽ እላታለሁ፤’ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ። |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት በድካሙም ለሰውነቱ መልካም ነገር ከሚያሳያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።
እነሆም፥ በዓልን፥ ደስታንና ሐሴትን አደረጋችሁ፤ በሬዎችንና በጎችንም አረዳችሁ፤ “ነገ እንሞታለን፤ እንብላ፤ እንጠጣም፤” እያላችሁ ሥጋን በላችሁ፤ ወይንንም ጠጣችሁ።
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።
እርሱም አለ፦ እንዲህ አደርጋለሁ፤ የቀድሞውን ጎተራዬን አፈርሳለሁ፤ ከእርሱ የሚበልጥ ሌላ ጎተራም እሠራለሁ፤ እህሌንና በረከቴንም በዚያ እሰበስባለሁ።
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።
በውኑ በኤፌሶን ከአውሬ ጋር የታገልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠቅመኛል? ሙታን የማይነሡ ከሆነ እንግዲህ እንብላ እንጠጣ፥ ነገም እንሞታለን።
እነዚህም ፍጻሜያቸው ለጥፋት የሆነ፥ ሆዳቸውን የሚያመልኩ፥ ክብራቸውም ውርደት የሆነባቸው፥ ምድራዊዉንም የሚያስቡ ናቸው።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥
ወደ እዚያም ባደረሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተነሣ በልተው፥ ጠጥተው፥ የበዓልም ቀን አድርገው፥ በምድር ሁሉ ላይ ተበትነው አገኛቸው።