ዘሌዋውያን 7:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኖሪያዎቻችሁ ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን አትብሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየትኛውም ቦታ ብትኖሩ የማንኛውንም የወፍ ዘር ወይም የእንስሳ ደም አትብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማደሪያዎቻችሁም ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን ፈጽሞ አትብሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እስራኤላውያን የትም ቦታ ቢኖሩ በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ የወፍም ሆነ የእንስሳ ደም አይብሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማደሪያዎቻችሁም ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን አትብሉ። |
እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፤ ዐይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፥ ደሙንም ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም።
ነገር ግን ለጣዖት ከሚሠዋው፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደም ከመብላት እንዲርቁ፥ ለራሳቸው የሚጠሉትንም በወንድሞቻቸው ላይ እንዳያደርጉ እዘዙአቸው።
ለአማልክት የተሠዋውን፥ ሞቶ የተገኘውን፥ ደምንም አትብሉ፤ ከዝሙትም ራቁ፤ በራሳችሁ የምትጠሉትንም በወንድሞቻችሁ ላይ አታድርጉ፥ ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”