እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
ዘሌዋውያን 6:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልጆቹም በእርሱ ፋንታ የተቀባው ካህን ያቀርበዋል። ለዘለዓለም ሥርዐት ነው፤ ሁልጊዜም ይደረጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱ ቦታ ተቀብቶ ካህን የሚሆነው ልጁ ይህን ያዘጋጅ፤ ለእግዚአብሔር የተመደበ ድርሻ ነውና ፈጽሞ ይቃጠል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልጆቹም መካከል በአባቱ ፋንታ የተቀባው ካህን ያዘጋጀዋል። ለዘለዓለም ሥርዓት እንዲሆን ፈጽሞ ለጌታ ይቃጠላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአሮን ተወላጆች መካከል ተቀብቶ የክህነትን ሥልጣን የሚረከብ ያን ያዘጋጃል፤ ያም የእግዚአብሔር ቋሚ ድርሻ ስለ ሆነ በሙሉ መቃጠል አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከልጆቹም በአባቱ ፋንታ የተቀባው ካህን ያቀርበዋል። ለዘላለም ሥርዓት እንዲሆን ፈጽሞ ለእግዚአብሔር ይቃጠላል። |
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
በፍየሉም ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ እርሱ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።
ካህኑም የተልባ እግር ቀሚስና የተልባ እግር ሱሪ በሰውነቱ ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።
ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ያደርጉታል፤ ለውሰውም ያገቡታል፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚፈተት መሥዋዕት ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።
“የእስራኤልም ልጆች የማስቢ ወገን ከሚሆን ከኢያቅም ልጆች ቦታ ከቤሮስ ተጓዙ። በዚያም አሮን ሞተ፤ ተቀበረም፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ።