ዘሌዋውያን 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቀደሰውንም የተልባ እግር ቀሚስ ይልበስ፤ የተልባ እግርም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፤ የተልባ እግር መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የተልባ እግር አክሊልም በራሱ ላይ ያድርግ፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በሰውነቱ ላይ የሚያርፈውን ከበፍታ የተሠራውን የውስጥ ሱሪ ያጥልቅ፤ የበፍታውን መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የበፍታውን መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ ልብሶቹ የተቀደሱ በመሆናቸው እነዚህን ከመልበሱ በፊት ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን ታጥቦ የክህነት ልብሱን ይልበስ፤ ይኸውም ከበፍታ የተሠራውን ቀሚስና ሱሪ ይልበስ፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራውን ቀበቶ ይታጠቅ፤ ከበፍታ የተሠራውንም መጠምጠሚያ ራሱ ላይ ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ የበፍታውንም መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው። |
ወደ ምስክሩ ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መሥዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል።
ነገራችን በፊቱ እንደ ሕፃን፥ በደረቅ መሬትም እንዳለ ሥር ሆነ፤ መልክና ውበት የለውም፤ እነሆ፥ አየነው፤ ደም ግባት የለውም፤ ውበትም የለውም።
ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፤ በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑሩት፤ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላውን ልብስ ይልበሱ።
እነሆም እያንዳንዳቸው ገጀሞ መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፤ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰና የሰንፔር መታጠቂያ በወገቡ የታጠቀ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
“አሮንም ወደ ምስክሩ ድንኳን ይገባል፤ ወደ መቅደሱም በገባ ጊዜ የለበሰውን የተልባ እግር ልብስ ያወልቃል፤ በዚያም ይተወዋል።
በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፤ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ለካህናቱ እንዳስተሰረየ ለራሱም፥ ለሕዝቡም ያስተሰርያል።
የሚቀባውም፥ በአባቱም ፋንታ ካህን ሊሆን የሚካነው ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የተልባ እግር ልብስ ይልበስ።
ካህኑም የተልባ እግር ቀሚስና የተልባ እግር ሱሪ በሰውነቱ ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።
ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ስለዚህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢአትን ለመሥራት ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ በሐሰት ቢምል፥
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
ልጆች በሥጋና በደም አንድ ናቸውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእነርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእነርሱም እንደ ወንድም ሆነላቸው፤ መልአከ ሞትን በሞቱ ይሽረው ዘንድ፥ ይኸውም ሰይጣን ነው።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።