ዘፀአት 30:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ወደ ምስክሩ ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መሥዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ሁሉ እንዳይሞቱ በውሃ ይታጠቡ፤ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የእሳት መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ፣ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም ለጌታ የእሳት መሥዋዕት ሊያቃጥሉ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠቡ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ይህንንም ማድረግ ያለባቸው ወደ ድንኳኑ ከመግባታቸውና የሚቃጠል መሥዋዕት ከማቅረባቸው በፊት ነው፤ ይህንንም ካደረጉ ከሞት ይድናሉ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መስዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ፥ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል። Ver Capítulo |