Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 30:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህንንም ማድረግ ያለባቸው ወደ ድንኳኑ ከመግባታቸውና የሚቃጠል መሥዋዕት ከማቅረባቸው በፊት ነው፤ ይህንንም ካደረጉ ከሞት ይድናሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ሁሉ እንዳይሞቱ በውሃ ይታጠቡ፤ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የእሳት መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም ለጌታ የእሳት መሥዋዕት ሊያቃጥሉ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ሳት መሥ​ዋ​ዕት ያቃ​ጥሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሊያ​ገ​ለ​ግሉ በቀ​ረቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መስዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ፥ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:20
14 Referencias Cruzadas  

ዑዛ ታቦቱን በመንካቱ እግዚአብሔር ተቈጥቶ ወዲያውኑ በሞት ቀሠፈው፤ ስለዚህም ዑዛ በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ፤


በሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤ መካከል እግዚአብሔር የተፈራ ነው፤ በዙሪያውም ካሉት ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል።


አሮንና ልጆቹ በዚህ ውሃ እጃቸውንና እግራቸውን ለመታጠብ ይጠቀሙበት።


ስለዚህ እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ፤ ይህም እነርሱና ከእነርሱ በኋላ የሚነሡት ዘሮቻቸው ለዘለዓለም የሚጠብቁት ቋሚ ሥርዓት ነው።”


ሙሴ፥ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በዚያ ታጠቡ፤


“አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን ታጥቦ የክህነት ልብሱን ይልበስ፤ ይኸውም ከበፍታ የተሠራውን ቀሚስና ሱሪ ይልበስ፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራውን ቀበቶ ይታጠቅ፤ ከበፍታ የተሠራውንም መጠምጠሚያ ራሱ ላይ ያድርግ።


ሙሴም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቅርቦ በውሃ አጠባቸው፤


እርስዋም በድንገት በእግሩ ሥር ወደቀችና ሞተች፤ ጐልማሶችም ሲገቡ ሞታ አገኙአትና ወስደው በባልዋ አጠገብ ቀበሩአት።


ሐናንያ ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ወደቀና ሞተ፤ ይህን ነገር የሰሙ ሰዎች ሁሉ እጅግ ፈሩ።


የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos