ሰቈቃወ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጐልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፤ ልጆችም በእንጨት ደከሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወጣት ወንዶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ ወንዶች ልጆች እንጨት በመሸከም ተንገዳገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ። |
በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።
በግብፅም ሀገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ አገልጋዪቱ በኵር ድረስ፥ የከብቱም በኵር ሁሉ ይሞታል።
ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወንድሞቹም ወጣ፤ መከራቸውንም ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው ከወንድሞቹ ከእስራኤል ልጆች አንዱን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ።
ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለም ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን የበደልን እስራት ፍታ፤ ጠማማውን ሁሉ አቅና፤ የተጨነቀውንም ሁሉ አድን፤ የዐመፃ ደብዳቤንም ተው።
ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጎቻ እንዲያደርጉ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፤ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዐይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አውርደው በእግር ብረት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።