Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሰቈቃወ 5:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወጣት ወንዶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ ወንዶች ልጆች እንጨት በመሸከም ተንገዳገዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ጕልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጉልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ጐል​ማ​ሶች ወፍ​ጮን ተሸ​ከሙ፤ ልጆ​ችም በእ​ን​ጨት ደከሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ጕልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 5:13
11 Referencias Cruzadas  

ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤


ከባድና አስቸጋሪ ሸክም አስረው በሰው ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤ ራሳቸው ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይፈልጉም።


“እኔ የምደሰትበት ጾም የጭቈና ሰንሰለትና የፍትሕ መጓደል ቀንበር ታላሉ ዘንድ፥ ቀንበሩን ሰብራችሁ የተጨቈኑትን ነጻ ታወጡ ዘንድ አይደለምን?


እንግዲህ መጅ አንሥተሽ ዱቄት ፍጪ፤ ዐይነ ርግብሽን ግለጪ፤ ካባሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽን ከፍ አድርገሽ በተራቈተ ቅልጥም ወንዙን ተሻገሪ።


ሚስቴ ለሌላ ሰው ፈጫይ ሆና ታገልግል፤ መኝታዋም ከሌሎች ወንዶች ጋር ይሁን።


የሚጠላህ ሰው አህያ ከጭነቱ ክብደት የተነሣ ወድቆ ብታገኝ፥ አህያውን ከወደቀበት ለማንሣት እንዲችል እርዳው እንጂ አልፈኸው አትሂድ።


የዙፋኑ ወራሽ ከሆነው ከንጉሡ ልጅ ጀምሮ እህል በመፍጨት ከምታገለግል ድኻ ሴት እስከ ተወለደው ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የእንስሶች በኲር ሁሉ ይሞታል።


ሙሴ ባደገ ጊዜ ወገኖቹን ለመጐብኘት ሄደ፤ ከባድ ሥራ መሥራታቸውን ተመለከተ፤ እንዲያውም አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ ሲደበድብ አየ።


ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።


ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፤ ሴቶች ‘የሰማይ ንግሥት’ ለተባለችው ጣዖት ኅብስት ለመጋገር ሊጥ ያቦካሉ፤ እኔንም ለማስቈጣት ለሌሎች አማልክት የወይን ጠጅ መባ ያቀርባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios