“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቁ፥ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ስለእኔ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ስለቀሩትም እግዚአብሔርን ጠይቁ” ብሎ አዘዛቸው።
ሰቈቃወ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ተቃዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላጋራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ለዐይኑ የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፤ መዓቱንም እንደ እሳት አፈሰሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ ቀኝ እጁ ተዘጋጅታለች፤ ለዐይን ደስ የሚያሰኙትን ሁሉ፤ እንደ ጠላት ዐረዳቸው፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ላይ፣ ቍጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ በቀኝ እጁ የያዘውን በእኛ ላይ አነጣጠረ፤ በኢየሩሳሌም ከተማ የምንመካባቸውን ሁሉ ገደለ፤ ቊጣውንም እንደ እሳት አቀጣጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ። |
“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቁ፥ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ስለእኔ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ስለቀሩትም እግዚአብሔርን ጠይቁ” ብሎ አዘዛቸው።
በእጃቸው ሥራ ሁሉ ሊያስቈጡኝ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት አጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
ስለዚህ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አመጣባቸው፤ በዙሪያቸው አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፤ በልባቸውም አላስተዋሉም።
ድንኳኔም ተበዘበዘ፤ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆችና በጎችም የሉም ከእንግዲህ ወዲህ ለድንኳኔም ቦታ የለም ለመንጎችም መሰማሪያ የለም፤
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።
እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትደርስ ይሆናል፤ ሁሉም ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳይነድ ለአምላካችሁ ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም።
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም፤ ቀኑንም ሁሉ መከራ አጸናብኝ።
ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ።
ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፤ ጽኑ ቍጣውንም አፍስሶአል፤ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፤ መሠረቷንም በላች።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፤ ያጠፋውም ዘንድ በቍጣዬ የሚያሰጥም ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ።
ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባትም ሀገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ።
ብርም በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጥዋ ትቀልጣላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።”
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይላቸውን፥ የተመኩበትንም ደስታ፥ የዐይናቸውንም አምሮት፥ የነፍሳቸውንም ምኞት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥
“ቍጣዬንና መዓቴንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ፤ መዓቴንም በፈጸምሁባቸው ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ታውቂያለሽ።
በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብም ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ በሀገር የቀረውና የተከበበውም በራብ ይሞታል፤ እንዲሁ መዓቴን እፈጽምባቸዋለሁ።
ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሏችሁም ያሸንፉአችኋል። ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።
እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።