Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 30:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ረስ​ተ​ው​ሃል፤ አይ​ፈ​ል​ጉ​ህ​ምም፤ በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ በጠ​ላት ማቍ​ሰ​ልና በጨ​ካኝ ቅጣት አቍ​ስ​ዬ​ሃ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ጨካኝ ሰው እንደሚቀጣው ጠላትም እንደሚያቆስለው አቁስዬሃለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ወዳጆቻችሁ ሁሉ ረስተዋችኋል፤ እነርሱ እናንተን አይፈልጉአችሁም፤ ኃጢአታችሁ የበዛ፥ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ ስለ ሆነ፥ እንደ ጠላት መታኋችሁ፤ ያለ ርኅራኄም ቀጣኋችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፥ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 30:14
38 Referencias Cruzadas  

ቤት። በሌ​ሊት እጅግ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ እን​ባ​ዋም በጉ​ን​ጭዋ ላይ አለ፤ ከሚ​ያ​ፈ​ቅ​ሩ​አት ሁሉ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናት የለም፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋም ሁሉ ወነ​ጀ​ሉ​አት፤ ጠላ​ቶ​ችም ሆኑ​አት።


ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፥ የዐ​መ​ፃ​ቸ​ውም ብዛት ጸን​ቶ​አ​ልና አን​በሳ ከዱር ወጥቶ ይሰ​ብ​ራ​ቸ​ዋል፤ የበ​ረ​ሃም ተኵላ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ነብ​ርም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ ይተ​ጋል፤ ከዚ​ያም የሚ​ወጣ ሁሉ ይነ​ጠ​ቃል።


ምሕ​ረት የሌ​ላ​ቸው ሰዎች ደበ​ደ​ቡኝ፥ የገ​ረ​ፈ​ችኝ እጅም በረ​ታች።


ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።


ቍስ​ልህ የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆኖ​አ​ልና ስለ ስብ​ራ​ትህ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ? በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ ይህን አድ​ር​ጌ​ብ​ሃ​ለሁ።


በግ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ነፋስ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ወዳ​ጆ​ች​ሽም ተማ​ር​ከው ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ስለ ክፋ​ትሽ ሁሉ ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ፤ በወ​ዳ​ጆ​ች​ሽም ፊት ቷረ​ጃ​ለሽ።


አን​ቺስ ምን ታደ​ር​ጊ​ያ​ለሽ? ቀይ በለ​በ​ስሽ ጊዜ፥ በወ​ርቅ አን​ባ​ርም ባጌ​ጥሽ ጊዜ፥ ዐይ​ን​ሽ​ንም በኵል በተ​ኳ​ልሽ ጊዜ፥ በከ​ንቱ ታጌ​ጫ​ለሽ፤ ፍቅ​ረ​ኞ​ችሽ አቃ​ለ​ሉሽ፥ ነፍ​ስ​ሽን ይሹ​አ​ታል።


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


በታ​ላቅ ቍጣም ያዘኝ እንደ ጠላ​ትም ቈጠ​ረኝ።


እኔም ለኤ​ፍ​ሬም እንደ ነብር፥ ለይ​ሁ​ዳም ቤት እንደ አን​በሳ ደቦል እሆ​ና​ለ​ሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እወ​ስ​ድ​ማ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውም የለም።


እና​ታ​ቸው አመ​ን​ዝ​ራ​ለ​ችና፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውም፥ “እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና ውኃ​ዬን፥ ቀሚ​ሴ​ንና መደ​ረ​ቢ​ያ​ዬን፥ ዘይ​ቴ​ንና የሚ​ገ​ባ​ኝን ሁሉ የሚ​ሰ​ጡኝ ወዳ​ጆ​ችን እከ​ተ​ላ​ቸው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ” ብላ​ለ​ችና አሳ​ፈ​ረ​ቻ​ቸው።


ስለ​ዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ነፍ​ስሽ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ለ​የች ወዳ​ጆ​ች​ሽን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው በወ​ዳ​ጆ​ችዋ በአ​ሦ​ራ​ው​ያን እጆች አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋት።


ቆፍ። ወዳ​ጆ​ችን ጠራሁ፤ እነ​ር​ሱም ቸል አሉኝ፤ ካህ​ና​ቶ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ረቱ ዘንድ መብል ሲፈ​ልጉ በከ​ተማ ውስጥ ሳያ​ገኙ አለቁ።


እነሆ በይ​ሁዳ ቤት የቀ​ሩ​ትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ያወ​ጣሉ፤ እነ​ዚ​ያም ሴቶች፦ ባለ​ሟ​ሎ​ችህ አታ​ል​ለ​ው​ሃል፤ አሸ​ን​ፈ​ው​ህ​ማል፤ እግ​ሮ​ችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነ​ርሱ ከአ​ንተ ወደ ኋላ ተመ​ል​ሰ​ዋል ይላሉ።


ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።


ሐሰ​ቴም በእኔ ላይ ተነ​ሣች፤ በፊ​ቴም ተከ​ራ​ከ​ረ​ች​ብኝ።


በች​ግ​ርሽ ቀን በጮ​ኽሽ ጊዜ እስኪ ይታ​ደ​ጉሽ፤ እነሆ፥ ዐውሎ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ነፋ​ስም ሁሉን ያስ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋል። ወደ እኔ የሚ​ጠጉ ግን ምድ​ሪ​ቱን ይገ​ዛሉ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች ከታ​ና​ሽ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገ​ርን ብቻ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እኔን በእ​ጃ​ቸው ሥራ ከማ​ስ​ቈ​ጣት በቀር ሌላ ሥራ አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሥ​ራ​ች​ሁን ክፋ​ትና ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ርኵ​ሰት ይታ​ገሥ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚህ ምድ​ራ​ችሁ ባድማ፥ በረ​ሃና መረ​ገ​ሚያ ሆና​ለች፤ እስከ ዛሬም የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።


ቀስ​ትና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ይተ​ም​ማል፤ በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የባ​ቢ​ሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአ​ንቺ ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ።


የተ​ማ​ማ​ል​ሃ​ቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ዳር​ቻህ ሰደ​ዱህ፤ የተ​ስ​ማ​ሙ​ህም ሰዎች ተነ​ሡ​ብህ፤ አሸ​ነ​ፉ​ህም፤ በበ​ታ​ች​ህም አሽ​ክላ ዘረ​ጉ​ብህ፤ እነ​ር​ሱም ማስ​ተ​ዋል የላ​ቸ​ውም።


ወደ ታላ​ላ​ቆቹ እሄ​ዳ​ለሁ እና​ገ​ራ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ ያው​ቃ​ሉና።” እነ​ዚህ ግን ቀን​በ​ሩን በአ​ን​ድ​ነት ሰብ​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ቱ​ንም ቈር​ጠ​ዋል።


ይችን ከተማ የሚ​ወጉ ከለ​ዳ​ው​ያን ይመ​ጣሉ፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም በእ​ሳት ያነ​ድ​ዱ​አ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለበ​ዓል ያጠ​ኑ​ባ​ቸ​ውን፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸ​ውን ቤቶች ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።


ያረ​ክ​ሱ​ትም ዘንድ ስሜ በተ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን አኖሩ።


ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”


አሌፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠ​ቈ​ራት! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ክብር ከሰ​ማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍ​ጣ​ውም ቀን የእ​ግ​ሩን መረ​ገጫ አላ​ሰ​በም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios