ሰቈቃወ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፤ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፥ “ውጠናታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፤ አግኝተናታል አይተናትማል” ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣ አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤ ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤ እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤ የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤ ኖረንም ልናየው በቃን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ። |
ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም ያጠፉኝ ዘንድ በሽንገላ ይመክራሉ።
እግዚአብሔር በቀን ይቅርታውን ያዝዛል፥ በሌሊትም እርሱን ይናገራል፤ ከእኔ ዘንድ የሕይወቴ ብፅዐት ለእግዚአብሔር ነው።
ፈርሰሻልና፥ ፈጽመሽም ጠፍተሻልና በአንቺ ለሚኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆኚባቸዋለሽ፤ ያጠፉሽም ከአንቺ ይርቃሉ።
በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም አሳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለርግማንና ለጥፋት፥ ለማፍዋጫም፥ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፤ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠሩ እኛ አናሳርፋቸውም አሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የጠለቀውንና የሰፋውን፥ ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙ መጠጥን በሚጠጡ ሰዎችም ዘንድ መሳቂያና መሳለቂያ ትሆኛለሽ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ፍልስጥኤማውያን በቀልን አድርገዋልና፥ በቀላቸውንም አጽንተዋልና፥ እስራኤልም ለዘለዓለም ይጠፉ ዘንድ ነፍሳቸው ደስ ይላታልና፤
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በል፦ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ ደስ ብሎሃልና፤
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእጆችህ አጨብጭበሃልና፥ በእግሮችህም አሸብሽበሃልና፥ ሰውነትህም በእስራኤል ምድር ላይ ደስ ብሎአታልና፤
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤
በቍጣዬና በመቅሠፍቴ በተበቀልሁሽ ጊዜ በዙሪያሽ በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ትጨነቂያለሽ፤ ትደነግጫለሽም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።