ሰቈቃወ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል፤ ካህናቷም ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተማረኩ፤ እርስዋም በምሬት አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ደናግሎችዋም ተጨነቁ እርስዋም በምሬት አለች። |
የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነሆም የይሁዳን ከተሞች ባድማና የሰገኖ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ታላቅ መነዋወጥ መጥቶአል።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
በእናንተ ላይ ክፉዎች የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ፤ ይበሉአችኋል፤ እንስሶቻችሁንም ያጠፋሉ፤ እናንተንም ያሳንሳሉ፤ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ።