አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
ኢያሱ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “አትፍራ፤ አትደንግጥ፤ ተዋጊዎችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋይንም ንጉሥ፥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “አትፍራ፤ አትደንግጥ፤ ሰራዊቱን ሁሉ ይዘህ በመውጣት ጋይን ውጋ፤ የጋይን ንጉሥ፣ ሕዝቡን፣ ከተማውንና ምድሩን አሳልፌ በእጅህ ሰጥቼሃለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፥ አትደንግጥ፤ ተዋጊዎቹን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፥ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እይ፥ የጋይን ንጉሥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ ሰጥቼሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “የጦር ወታደሮችህን ይዘህ ወደ ዐይ ከተማ ለመዝመት ውጣ፤ ከቶ አትፍራ፤ ደፋር ሁን፤ እኔ በዐይ ንጉሥ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አድርጌሃለሁ፤ ሕዝቡ፥ ከተማይቱና ምድሪቱ የአንተ ይሆናሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ አትፍራ፥ አትደንግጥ፥ ሰልፈኞችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፥ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፥ እይ፥ የጋይን ንጉሥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ ሰጥቼሃለሁ። |
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዞችም አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
“ነገር ግን አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከተማረኩባት ምድር አድናለሁ፤ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል፤ ተዘልሎም ይተኛል፤ ማንም አያስፈራውም።
ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሽላት፤ እናንተም የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም፥ ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፤ ማቅም ታጠቁ፤ አልቅሱም።
እነሆ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ምድሪቱን በፊታችሁ እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፤ ውረሷት፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አይጥልህም፤ አይተውህም፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ’ ” አለው።
ከፊታቸው አትደንግጥ፤ አምላክህ እግዚአብሔር፥ ከአንተ ጋር ነውና፥ እርሱም አምላክህ እግዚአብሔር ታላቅና ጽኑዕ ነውና።
እነሆ አዝዝሃለሁ፤ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም።”
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው በፊትህ የሚተርፍ የለም፤” አለው።
ኢያሱንም፥ “በእውነት እግዚአብሔር ሀገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ በዚያች ምድር የሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ከእኛ የተነሣ ደነገጡ” አሉት።
ከነዓናውያንም፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፤ ከምድርም ያጠፉናል፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?”