ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
ኢያሱ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤ በድንጋይም ወገሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም፣ “እንዲህ ያለውን መከራ ለምን አመጣብህን? እነሆ፤ ዛሬ በአንተም ላይ እግዚአብሔር መከራ ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤል በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤ የቀሩትንም እንደዚሁ ከወገሩ በኋላ በእሳት አቃጠሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም፦ “ለምን መከራን አመጣህብን? ጌታ ዛሬ መከራን ያመጣብሃል” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔር ዛሬ ያስጨንቅሃል አለው፥ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፥ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው። |
ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
እንዲህም ሆነ፤ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ፥ “ምራትህ ትዕማር ሴሰነች፤ እነሆ፥ በዝሙት ፀነሰች” ብለው ነገሩት። ይሁዳም፥ “አውጡአትና በእሳት ትቃጠል” አለ።
መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።
ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ኀጢአት ነው፤ በመካከላቸው ኀጢአት እንዳይሆን እርሱንና እነርሱን በእሳት ያቃጥሉአቸው።
“ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የሀገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገሩት።
“ተሳዳቢውን ከሰፈር ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት።”
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና በድንጋይ ይውገሩት፤ ይግደሉትም።
ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትመትዋቸዋላችሁ።
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
አስተውሉ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ የሚያቃልል አይኑር፤ ሕማምን የምታመጣ፥ ብዙዎችንም የምታስታቸውና የምታረክሳቸው መራራ ሥር የምትገኝበትም አይኑር።
እናንተ ግን እርም ብለን ከተውነው እንዳትወስዱ ተጠንቀቁ፤ ከእርሱም ተመኝታችሁ አትውሰዱ፤ ብትወስዱ ግን የእስራኤልን ሰፈር የተረገመች ታደርጓታላችሁ፤ እኛንም ታጠፉናላችሁ።
ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።”