ዮሐንስ 11:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያችም ቀን ጀምሮ የካህናት አለቆች ሊገድሉት ተማከሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ቀን ጀምሮም፣ ሊገድሉት አሤሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስን ለመግደል ተማከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ። |
እኔም አስመሰከርሁባቸውና፥ “ከቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደ ገና ብታደርጉት እጆችን አነሣባችኋለሁ” አልኋቸው። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ በሰንበት ቀን እንደ ገና አልመጡም።
ከዚያም ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ብላቴኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩሌቶቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስትና ጥሩርም ይዘው በፊትና በኋላ ይጠብቁ ነበር፤ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።
አለቆቹም ንጉሡን፥ “ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚያች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ፥ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።
የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ጉባኤውን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ያደርጋል፤ ምን እናድርግ?
ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ በገሊላ ይመላለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድርም ሊሄድ አልወደደም፤ አይሁድ ሊገድሉት ይሹ ነበርና።