ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም።
ኢዮብ 41:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአፉ የሚቃጠል መብራት ይወጣል የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፤ ማን ፊቱ ሊቆም ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲያስነጥስ ብልጭታ ያወጣል፥ ዐይኖቹም እንደ ንጋት ወገግታ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ላይ አደጋ መጣል ይህን ያኽል አደገኛ ከሆነ፥ ታዲያ፥ እኔን ለመቃወም የሚደፍር ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጥሽታው ብልጭታ ያወጣል፥ ዓይኖቹም እንደ ወገግታ ናቸው። |
ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም።
እግሮችህ ሮጠው ይደክማሉ፤ ፈረሶችን ለምን ታስጌጣለህ? በሰላምም ምድር ላይ ለምን ትታመናለህ? በዮርዳኖስስ ጩኸት ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?”
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና እንደ አንበሳ ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወጣል፤ ጐልማሶቹንም ሁሉ በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቋቋም እረኛ ማን ነው?
አርፎአል፥ እንደ አንበሳና እንደ አንበሳ ደቦል ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቁህ ሁሉ የተመረቁ ይሁኑ፤ የሚረግሙህም ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ።”