Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኢዮብ 41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “እነሆ፥ ተስፋ ማድረግ ከንቱ ነው፥ እርሱን ማየቱ ብቻ ያብረከርካል።

2 ማንም ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው?

3 እመልስለትስ ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማን ነው? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው።

4 ስለ አካላቱና ስለ ብርቱ ኃይሉ፥ ስለ መልካም ሰውነቱም ዝም አልልም።

5 የውጪ ልብሱን ማን ይገፋል? በጥንድ መንጋጋውስ ውስጥ ማን ይገባል?

6 የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው? በጥርሶቹ ዙሪያ ግርማ አለ።

7 የጀርባው ቆዳዎች ጠንካራ ናቸው፤ አቤት ኩራት! በጥብቅ ማተሚያ እንደ ታተሙ ናቸው።

8 እርስ በርሳቸው የተቀራረቡ ናቸውና ነፋስ በመካከላቸው መግባት አይችልም።

9 እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፥ እስከማይለያዩም ድረስ ተያይዘዋል።

10 ሲያስነጥስ ብልጭታ ያወጣል፥ ዐይኖቹም እንደ ንጋት ወገግታ ናቸው።

11 ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥ የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።

12 እንደ ፈላ ድስትና እንደሚቃጠል ሸምበቆ ከአንፍንጫው ጢስ ይወጣል።

13 እስትንፋሱ ከሰልን ታቃጥላለች፥ ነበልባልም ከአፉ ይወጣል።

14 አንገቱ በጣም ጠንካራ ነው፥ ግርማ በፊቱ ይዘፍናል።

15 ሥጋውም እርስ በርስ የተጣበቀ ነው፥ ምንም ላያንቀሳቅሳቸው በእርሱ ላይ ጸንተዋል።

16 ልቡ እንደ ድንጋይ የደነደነ ነው፥ እንደ ወፍጮ ድንጋይ የጸና ነው።

17 በተነሣ ጊዜ ኃያላን ይፈራሉ፥ ከድንጋጤም የተነሣ ይናወጣሉ።

18 ሰይፍና ጦር፥ ፍላጻና መውጊያም ቢያገኙት አያሸንፉትም።

19 ብረትን እንደ ገለባ፥ ናስንም እንደ ነቀዝ እንጨት ይቆጥራል።

20 ቀስት ሊያባርረው አይችልም፥ የወንጭፍም ድንጋዮች እንደ ገለባ ይሆኑለታል።

21 ዱላን እንደ ገለባ ይቈጥረዋል፥ ሰይፎች ሲንቀጠቀጡ ይስቃል።

22 የአካሉ ታችኛው ክፍል እንደ ስለታም ገል ነው፥ እንደ መዳመጫም በጭቃ ላይ ያልፋል።

23 ቀላዩን እንደ ድስት ያፈላዋል፥ ባሕሩንም እንደ ሽቱ ምንቸት ያደርገዋል።

24 በስተ ኋላው ብሩህ መንገድን ያበራል፥ ቀላዩም ሽበት ይመስላል።

25 ያለ ፍርሃት የተፈጠረ፥ እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።

26 ከፍ ያለውን ሁሉ ይመለከታል፥ በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos