ንጉሡም የካህናቱን አለቃ ኬልቅያስን በሁለተኛውም መዓርግ ያሉትን ካህናት በረኞቹንም፥ ለበዓልና ለማምለኪያ ዐፀድ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ከኢየሩሳሌምም ውጭ በቄድሮን ሜዳ አቃጠሉት፤ አመዱንም ወደ ቤቴል ወሰዱት።
ኤርምያስ 52:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዦቹም አለቃ ታላቅን ካህን ሠራያን፥ ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን፥ ሦስቱንም በረኞች ወሰደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብር ዘበኞቹ አዛዥም ሊቀ ካህኑን ሠራያን፣ በማዕርግ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የበር ጠባቂዎች አስሮ ወሰዳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን በማዕረጉም ሁለተኛ የነበረውን ካህን ሶፎንያስን የደጃፉም ጠባቂዎች የነበሩትን ሦስቱን ሰዎች ወሰደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ሁሉ ጋር የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሠራያን፥ በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሌሎችንም ሦስት የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎችን አስሮ ወሰደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ፥ |
ንጉሡም የካህናቱን አለቃ ኬልቅያስን በሁለተኛውም መዓርግ ያሉትን ካህናት በረኞቹንም፥ ለበዓልና ለማምለኪያ ዐፀድ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ከኢየሩሳሌምም ውጭ በቄድሮን ሜዳ አቃጠሉት፤ አመዱንም ወደ ቤቴል ወሰዱት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ አንተን ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር አፈልስሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤ ዐይኖችህም ያያሉ፤ አንተንና ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና የካህኑን የመዕሴይን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እንዲህም አለ፦
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወደ አለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ ማሴው ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስሜ እንዲህ ስትል ልከሃል፦
የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ለጠላቶቻቸው እጅ፤ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።
ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በማሴው ጓዳ በላይ ባለው በአለቆቹ ጓዳ አጠገብ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጎዶልያ ልጅ ወደ ሐናንያ ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።
ንጉሡም ሴዴቅያስ፥ “ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የማሴውን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።
በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመተ መንግሥት በአምስተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
የአዛዦቹም አለቃ ናቡዛርዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የሕዝቡንም ቅሬታ አመጣ።
ዔ። የእግዚአብሔር ፊት ክፍላቸው ነበረ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፤ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፤ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ያኖራችኋቸው ግዳዮቻችሁ እነርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህችም ከተማ ድስት ናት፤ እናንተን ግን ከመካከልዋ አወጣችኋለሁ።
ከመንጋው የተመረጠውን ውሰድ፤ አጥንቶቹም እንዲበስሉ በበታችዋ እሳት አንድድ፤ አፍላው፤ በእጅጉ ይፍላ፤ አጥንቶቹም በውስጥዋ ይቀቀሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ፤ በጎችንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፤ በጎችንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ፤ ከዚያም ወዲያ እረኞች በጎችን አያሰማሩም፤ በጎችንም ከአፋቸው አድናለሁ፤ መብልም አይሆኑላቸውም።