Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 29:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህ​ኑም ወደ ማሴው ልጅ ወደ ሶፎ​ን​ያስ፥ ወደ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን በስሜ እን​ዲህ ስትል ልከ​ሃል፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኢየሩሳሌም ላለው ሕዝብ ሁሉ፣ ለካህኑ ለመዕሤያ ልጅ ለሶፎንያስና ለሌሎችም ካህናት ሁሉ በገዛ ስምህ ደብዳቤዎችን ልከሃል፤ ለሶፎንያስም እንዲህ ብለሃል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 29:25
16 Referencias Cruzadas  

የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ታላ​ቅን ካህን ሠራ​ያን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ካህን ሶፎ​ን​ያ​ስን፥ ሦስ​ቱ​ንም በረ​ኞች ወሰደ፤


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰ​ሌ​ም​ያን ልጅ ዮካ​ል​ንና ካህ​ኑን የማ​ሴ​ውን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ ላከ።


ካህ​ኑም ሶፎ​ን​ያስ ይህን ደብ​ዳቤ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ ጆሮ አነ​በ​በው።


ምን​አ​ል​ባት በመ​ን​ገድ የሚ​ያ​ገ​ኘው ሰው ቢኖር ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰረ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ላሉት ምኵ​ራ​ቦች የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ ከሊቀ ካህ​ናቱ ለመነ።


ደግ​ሞም በፊቴ ስለ እርሱ መል​ካ​ም​ነት ይና​ገሩ ነበር፤ የእ​ር​ሱን ነገር ወደ እኔ ያመጡ ነበር፤ የእ​ኔ​ንም ቃል ወደ እርሱ ይወ​ስዱ ነበር፤ ጦቢ​ያም ሊያ​ስ​ፈ​ራ​ራኝ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልክ ነበር።


በዚ​ያም ወራት ብዙ የይ​ሁዳ አለ​ቆች ወደ ጦብያ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልኩ ነበር፤ የጦ​ብ​ያም ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ወደ እነ​ርሱ ይመጡ ነበር።


ሰን​ባ​ላ​ጥም እንደ ፊተ​ኛው ብላ​ቴ​ና​ውን አም​ስ​ተኛ ጊዜ ላከ​ብኝ፤ በእ​ጁም ውስጥ እን​ዲህ የሚል ግልጥ ደብ​ዳቤ ነበረ፦


ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እየ​ተ​ገ​ዳ​ደረ በእ​ር​ሱም ላይ እየ​ተ​ና​ገረ፥ “የም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እን​ዳ​ል​ቻሉ፥ እን​ዲሁ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ አም​ላክ ሕዝ​ቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይ​ች​ልም” የሚል ደብ​ዳቤ ጻፈ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ከመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ተቀ​ብሎ አነ​በ​በው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘረ​ጋው።


እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊወ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመ​ልሶ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦


ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ወደ ተረ​ፉት የም​ርኮ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ ካህ​ና​ቱም፥ ወደ ሐሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያ​ቱም፥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ሰ​ውም ሕዝብ ሁሉ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የላ​ከው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios