“በእነርሱ ላይ እነሣለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም አጠፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
ኤርምያስ 50:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፤ እነሆ በአሕዛብ መካከል ኋለኛዪቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረሀም ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትዋረዳለች። እርሷም ምድረ በዳ፣ ደረቅ ምድርና በረሓ፣ ከመንግሥታትም ሁሉ ያነሰች ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትዋረዳለች፤ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ታላቂቱ ከተማችሁ በጣም ታፍራለች፤ እናት አገራችሁም ትዋረዳለች፤ ከመንግሥታት ሁሉ ያነሰች ትሆናለች። ውሃ የማይገኝባት ሆና ወደ ምድረ በዳነት ትለወጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፥ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፥ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች። |
“በእነርሱ ላይ እነሣለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም አጠፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
ሰባት የወለደች ባዶ ቀረች፤ ነፍስዋም ተጨንቃለች፤ በቀትር ጊዜ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች፤ ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፤ በርግጥ ምድረ በዳና ማንም የማይቀመጥባቸው ከተሞች አደርግሃለሁ።
“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ።
የቀረቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፤ የሲሳርም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።
ስለዚህ እነሆ በአሞን ልጆች ከተማ በራባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለጥፋትም ትሆናለች፥ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎንን ምስሎች የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፤ ምድርዋም ሁሉ ትደርቃለች፤ ተዋግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።