ኤርምያስ 47:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል፤ አስቀሎና ጠፋች፤ የዔናቅ ቅሬታዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትነጫላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፤ አስቀሎና አፏን ትይዛለች። በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ቅሬታዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቷል፤ አስቀሎና በጸጥታ ተውጣለች፤ በሸለቆ ያላችሁ ትሩፋን ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትተለትላላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋዛ ሕዝብ በሐዘን ጠጒራቸውን ይላጫሉ፤ የአስቀሎና ሕዝብ ሁሉ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ። በፍልስጥኤም ሸለቆ ከጥፋት የተረፉትስ ሰውነታቸውን እየቈራረጡ የሚያዝኑት እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል፥ አስቀሎና ጠፋች፥ የዔናቅ ቅሬታዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትነጫላችሁ? |
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
ታላላቆችና ታናናሾች በዚች ምድር ይሞታሉ ፥ አይቀበሩም ሰዎችም አያለቅሱላቸውም፤ ስለ እነርሱም ፊት አይነጩላቸውም፤ ራስንም አይላጩላቸውም፤
የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፤ አስቀሎናንም፥ ጋዛንም፥ አቃሮንንም፥ የአዛጦንንም ቅሬታ፤
ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ።
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮስንና ሲዶናን የቀሩትንም ረዳቶቻቸውን ታጠፋ ዘንድ ስለምትመጣው ቀን ነው፤ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንንና በከፍቶር ደሴት የቀሩትን ያጠፋልና።
በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃነት አለ፤ ጽሕማቸውን ሁሉ ይላጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ሁሉም በወገባቸው ማቅን ይታጠቃሉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍልስጥኤማውያን ላይ እዘረጋለሁ፤ መኳንንቱንም እቈርጣለሁ፤ የባሕሩንም ዳር ቅሬታ አጠፋለሁ።
ማቅም ትታጠቃላችሁ፤ ድንጋጤም ይሸፍናችኋል፤ በፊትም ሁሉ ላይ ሐፍረት ይሆናል፤ በራሳችሁም ሁሉ ላይ ቡሃነት ይሆናል።
ይሁዳም ጋዛንና አውራጃዋን፥ አስቀሎናንና አውራጃዋን፥ አቃሮንንና አውራጃዋን፥ አዛጦንንና አውራጃዋን አልወረሳትም።