ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክዩንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሓፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓስያን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦
ኤርምያስ 39:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስንም ከግዞት ቤቱ አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልከው ኤርምያስን ከዘበኞች አደባባይ አስወጡት፤ የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ ቤቱ እንዲወስደው በዐደራ ሰጡት፤ ኤርምያስም በራሱ ሕዝብ መካከል ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልከው ኤርምያስን ከእስር ቤት አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም እንዲወስደው ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እርሱም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታስሬበት ከነበረው በቤተ መንግሥቱ ግቢ ከሚገኘው ዘብ ጠባቂዎች ክፍል እንድወጣ አስደረገ፤ እኔም የሳፋን የልጅ ልጅ በሆነው በአሒቃም ልጅ በገዳልያ እጅ ወደ ቤቴ ተወሰድኩ፤ እኔም ከሕዝቤ ጋር በዚያ ኖርኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስንም ከግዞት ቤት አደባባይ አወጡት፥ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፥ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ። |
ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክዩንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሓፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓስያን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦
እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በዚያ በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ለእርስዋም ነገሩአት።
ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ አብዶንን፥ ጸሓፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዔሴኢያን፦
ንጉሡም ኢዮአቄም ሰዎችን ወደ ግብፅ ላከ፤ የአክቦርን ልጅ ኤልናታንን፥ ሌሎችንም ሰዎች ከርሱ ጋራ ወደ ግብፅ ላካቸው።
በዚያ ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።
ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፤ ኤርምያስንም በግዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖሩት፤ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከውጪ ጋጋሪዎች እያመጡ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀምጦ ነበር።
የአዛዞች አለቃ ናቡዛርዳንም ላከ፤ ናቡሻዝባንም፥ ራፋስቂስም፥ ኔርጋል ሴራአጼርም፥ ራብማግም፥ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ ላኩ።
ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን በሰንሰለት አስሮ በወሰደው ጊዜ ከራማ ከለቀቀው በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።
እርሱም ገና ሳይመለስ፥ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ፤ ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል በይሁዳ ምድር ተቀመጥ፤ ወይም ትሄድ ዘንድ ለዐይንህ ደስ ወደሚያሰኝህ ስፍራ ሂድ” አለው። የአዛዦችም አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው።
ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ አለበት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር በሀገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
በየሜዳው የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሀገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትንም የምድርን ድሆች እንዳስጠበቀ በሰሙ ጊዜ፥
እንዲህም ሆነ፤ በሰባተኛው ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ መሴፋ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በመሴፋ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ።