እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፥ “በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንግባ፤ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፤ እነርሱ በሌሊት ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና” አለኝ።
ኤርምያስ 36:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፥ “እኔ እስረኛ ነኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤትም እገባ ዘንድ አልችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ አለው፤ “እኔ ተከልክያለሁና ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግባት አልችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “እኔ ተከልክያለሁ፤ ወደ ጌታ ቤት ለመግባት አልችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ለባሮክ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠሁት፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት አይፈቀድልኝም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ እኔ ተግዤአለሁ፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እገባ ዘንድ አልችልም። |
እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፥ “በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንግባ፤ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፤ እነርሱ በሌሊት ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና” አለኝ።
ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን ገረፈው፤ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው አዘቅት ውስጥ ጣለው።
የአጎቴም ልጅ አናምኤል፥ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፥ በግዞት ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድም ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለማሴው ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።
በዚያ ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በግዞት ቤትም አደባባይ ወደ ነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።
አሁንም እነሆ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፤ እኔም በመልካም አይሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፤ ተመልከት፥ እነሆ፥ ሀገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ በሚታይህና ደስ በሚያሰኝህም ስፍራ ተቀመጥ።”
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ቢሆኑም እኔም እንደ ሰነፍ ለራሴ እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ እጅግም ደከምሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገረፍሁ፤ ብዙ ጊዜም ታሰርሁ፤ ብዙ ጊዜም ለሞት ተዘጋጀሁ።