Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 36:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህም በኋላ ለባሮክ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠሁት፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት አይፈቀድልኝም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ አለው፤ “እኔ ተከልክያለሁና ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግባት አልችልም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “እኔ ተከልክያለሁ፤ ወደ ጌታ ቤት ለመግባት አልችልም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኤር​ም​ያ​ስም ባሮ​ክን እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፥ “እኔ እስ​ረኛ ነኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም እገባ ዘንድ አል​ች​ልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ እኔ ተግዤአለሁ፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እገባ ዘንድ አልችልም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 36:5
15 Referencias Cruzadas  

በዚህም ጊዜ ከቤቱ እንዳይወጣ ተዘግቶበት ወደነበረው የመሄጣብኤል የልጅ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ደላያ ልጅ ሸማዕያ ዘንድ ሄድኩ፤ እርሱም “በሌሊት ሊገድሉህ ስለሚመጡ አንተና እኔ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተን በሮቹን በመዝጋት እንደበቅ” አለኝ።


ወዳጆቼ ሁሉ ከእኔ እንዲርቁ አደረግህ፤ በፊታቸውም አጸያፊ አደረግኸኝ፤ ዙሪያዬ ታጥሮአል፤ ማምለጫም የለኝም።


ተይዤ እንድደበደብ አዘዘ፤ ከቤተ መቅደሱም በላይኛው በኩል ባለው በብንያም የቅጽር በር በእግር ግንድ እንድታሰር አደረገ።


የማሕሴያ የልጅ ልጅ ለሆነው ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት፤ እነዚያን ግልባጮች የሰጠሁት በሐናምኤል፥ የሽያጩን ውል በፈረሙት ምስክሮችና በአደባባዩ ተቀምጠው በነበሩት ሰዎች ፊት ነው፤


ያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ከበባ ያደረገበት ጊዜ ነበር፤ እኔም በዚያን ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ነበር፤


በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ገና ታስሬ እንዳለሁ የእግዚአብሔር ቃል እንደገና መጣልኝ፤


እነርሱም በብርቱ ተቈጥተው ካስደበደቡኝ በኋላ የእስር ቤት እንዲሆን አድርገውት ወደነበረው ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት ውስጥ አስገብተው ዘጉብኝ፤


እኔም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ጊዜ ድረስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ቈየሁ።


ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።


እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”


እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እኔ ከእነርሱ ይበልጥ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፤ ይህንንም ስል እንደ እብድ ሆኜ ነው የምናገረው፤ ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት አደጋ ደርሼአለሁ፤


ስለዚህ እኔ ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ የሆንኩት ለእናንተ ለአሕዛብ ስል ነው።


አሁንም በሰንሰለት ታስሬ የዚሁ ወንጌል መልእክተኛ ነኝ፤ ስለዚህ እንደሚገባኝ ያለ ፍርሀት እንድናገር ጸልዩልኝ።


በዚህም ወንጌል ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በሰንሰለት ታስሬ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።


ሌሎች መዘባበቻ ሆነው ተገረፉ፤ ሌሎች በእግር ብረት ታስረው ወደ ወህኒ ቤት ተጣሉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos