የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
ኤርምያስ 32:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን ይመጣሉ፤ ከተማዋንም በእሳት ያነድዱአታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ያጠኑባቸውን፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸውን ቤቶች ያቃጥሉአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱን የሚወጓት ባቢሎናውያን ወደ ውስጥ ይገባሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤ ያስቈጡኝ ዘንድ ሕዝቡ በየሰገነቱ ላይ ለበኣል ያጠኑባቸውንና ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን ያቀረቡባቸውን ቤቶች ጭምር ያነድዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፥ እኔንም ለማስቈጣት በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ካጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችን ከተማ የከበቡ ባቢሎናውያን መጥተው ያቃጥሉአታል፤ እንደዚሁም እኔን ለማስቈጣት በጣራዎቻቸው ላይ ለባዓል ጣዖት ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትንና ለሌሎችም ጣዖቶች የመጠጥ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን ቤቶች ያቃጥላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፥ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል ካጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል። |
የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሰ፤ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠለ፤ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፋ።
ሕዝቡም ወጥተው አመጡ፤ እያንዳንዱም በቤቱ ሰገነት ላይ፥ በአደባባዩም ላይ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ላይ፥ በውኃውም በር አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳስ ሠሩ።
ለበዓልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ግንቦች ትበላለች፤ አትጠፋምም።
የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ፤ እነዚያም በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ።”
ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።”
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አስጠብቆት ነበርና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይቺን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ይይዛታል ብለህ ስለምን ትንቢት ትናገራለህ?
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፋ ትሰጣለች፤ ይይዛታል፤ በእሳትም ያቃጥላታል።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፦ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ፥ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ የተሳልነውን ስእለታችንን በርግጥ እንፈጽማለን አላችሁ፤ በእጃችሁም አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።
በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመተ መንግሥት በአምስተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፥ በእሳት አቃጠለ።
ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጎቻ እንዲያደርጉ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፤ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።
ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፤ ጽኑ ቍጣውንም አፍስሶአል፤ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፤ መሠረቷንም በላች።
ጉባኤውም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል፤ በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፤ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።