Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 7:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነ​ር​ሱስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ውስ​ጥና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አታ​ይ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱስ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ይልቅስ በኢየሩሳሌም መንገዶችና በይሁዳ ከተሞች የሚያደርጉትን ሁሉ አትመለከትምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነርሱስ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 7:17
11 Referencias Cruzadas  

መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን በአ​ያ​ችሁ ጊዜ ያጽ​ና​ኗ​ች​ኋል፤ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ት​ንም ሁሉ በከ​ንቱ እን​ዳ​ላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ባት ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በተ​ፈ​ታኝ ሕዝቤ መካ​ከል ፈታኝ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በፈ​ተ​ንሁ ጊዜ ታው​ቀ​ኛ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”


ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እን​ጎቻ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን እን​ዲ​ያ​ፈ​ስሱ ልጆች እን​ጨት ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ አባ​ቶ​ችም እሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ ሴቶ​ችም ዱቄት ይለ​ው​ሳሉ።


ስለ​ዚህ መዓ​ቴና መቅ​ሠ​ፍቴ ወረደ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ።


ስለ ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተዉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት ስለ ሠዉ፥ ለእ​ጃ​ቸ​ውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍር​ዴን በእ​ነ​ርሱ ላይ እና​ገ​ራ​ለሁ።


ይችን ከተማ የሚ​ወጉ ከለ​ዳ​ው​ያን ይመ​ጣሉ፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም በእ​ሳት ያነ​ድ​ዱ​አ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለበ​ዓል ያጠ​ኑ​ባ​ቸ​ውን፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸ​ውን ቤቶች ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።


ይህም እኔን ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ ስለ አደ​ረ​ጉት ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።


በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።


ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios