ኤርምያስ 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትጠገን ዘንድ ክርክርህን የሚፈርድልህ ሰው የለም፤ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኀኒት የለህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሟገትልህ ሰው የለም፤ ለቍስልህ መድኀኒት አይኖርም፤ ፈውስም አታገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙግትህን የሚፈርድልህ የለም፥ ለቁስልህም መድኃኒት የለውም፥ ለአንተም ፈውስ የለህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእናንተ የሚከራከርላችሁ የለም፤ ለቊስላችሁም መድኃኒት አይገኝም፤ እናንተም አትድኑም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትጠገን ዘንድ ክርክርህን የሚፈርድልህ የለም፥ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኃኒት የለህም። |
እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፤ አልተጠገነምም፤ በዘይትም አልለዘበም።
በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ስለ ምን ተስፋ አደረግን? ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም፤ የፈውስን ጊዜ ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ድንጋጤ ሆነ።
እኔ ከክፉ ቍስልሽ እፈውስሻለሁ፤ ጤናሽን እመልስልሻለሁ፤ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።”
እነሆ ፈውስንና መድኀኒትን እሰጣታለሁ፤ እፈውሳታለሁም፤ የሰላምንና የእውነትንም መንገድ እገልጥላቸዋለሁ።
ድንግሊቱ የግብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ፤ የሚቀባ መድኀኒትንም ውሰጂ፤ ለምንም የማይጠቅምሽን መድኀኒት በከንቱ አብዝተሻል።
በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋቷ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፤ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቷ አለ።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድንሻል? ማንስ ያጽናናሻል? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?
ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው ከእነርሱ መካከል ፈለግሁ፤ ነገር ግን አላገኘሁም።
“የሰው ልጅ ሆይ! የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፥ እነሆም ይድን ዘንድ መድኃኒት ቀብተው አያደርቁትም፤ ሰይፉንም ለመያዝ ኀይልን ያገኝ ዘንድ አልታሰረም።
አሦር አያድነንም፤ በፈረስም ላይ አንቀመጥም፤ ድሃአደጉም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ የእጆቻችንን ሥራ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም።”
በመከራቸው ጊዜ በማለዳ ወደ እኔ ይገሰግሳሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናልና፥ እርሱም ይጠግነናል።
ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።
ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።